በኡማህጅርና በታች በርማጭሆ በደቡብ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ውጊያ ተደረገ | በወልቃይት ገበሬዎች እና የውስጥ አርበኞች የሕወሓት ሰራዊትን መከቱ

 

 

clash

ከልዑል ዓለሜ

ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት….. ከትግራይ አስገዶ_ ጼምበላ እንዲሁም ከታህታይ አዲያቦ በመጡ ልዩ ሐይል እና ታጣቂዎች ቢወረሩም ቆራጡ የአማራ ኢትዮጵያዊ ገበሬና የዉስጥ አርበኞች አልበገር ባይነታቸዉን እያስመሰከሩ ይገኛሉ፡፡

በአካባቢዉ የሚኖሩ ልዩ ሐይልና ታጣቂዎችን ከማስጠንቀቅ አንጻር በቤተሰብ በኩል ከእኩይ ተግባራቸዉ እንዲቆጠቡ ተጠይቀዉ አሻፈርን ባሉ 3 ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰዱን ያሳወቁት የዉስጥ አርበኞች አያይዘዉ በዳንሻ፣ በሳንጃ፣ በሶርቃ፣ በወልቃይት ጠገዴ እና በጠለምት እንዲሁም በሁመራ ዙሪያ 29 ከትግራይ ክልል የመጡ ወራሪዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዳቸው ተሰምቷል::

በተያያዘ ዜና በትናንትናዉ እለት በወያኔና በነጻነት ሐይሎች መካከል በኡማህጅርና በታች በርማጭሆ በደቡብ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ከባድ ዉጊያ መደረጉን ታማኝ ምንጮች ጠቅሰዋል።

ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዚህ አካባቢ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል በተለያዩ ጊዜያት በሥርዓቱ ሰዎች ላይ እርምጃ ሲወስዱ ቆይተዋል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል:: ከኤርትራ ሙሉ በሙሉ ጠቅልሎ ወጥቷል የሚባለው ይኸው ንቅናቄ በጎንደር በኩል በተለያዩ ጊዜያት የሽምቅ ውጊያዎችን እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ እየተዘገበ ነው:: ንቅናቄው ሰሞኑን በወልቃይት ጠገዴ ጸለምት ዙሪያ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ተስተናግዷል::

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ /አዴሃን/ የተሰጠ አገራዊ ጥሪ
መጋቢት 14 ቀን 2008 ዓ• ም
ለአማራው ቆሜያለሁ፣ አማራውን ከጥቃት፣ ከውርደትና ከጉስቁልና እታደጋለሁ ብሎ በአማራ ህዝብ ትክሻ ላይ የተፈናጠጠው ብአዴን ማንነቱ የሚፈትንበት ታሪካዊ ጊዜ ተፈጥሯል። ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዳንሻ ላይ የተነሳው የማንነት ጥያቄ በህወኃት ልዩ ኃይልና በፌደራል ፓሊስና በመደበኛ ሰራዊት ሲደበደብ ዝምታ የመረጠው ብአዴን ከወያኔ ባልተናነሰ ሁኔታ የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት መሆኑን እያሳዬ ነው። እነ አባይ ወልዱ ለህዝባቸው ቀንና ሌሊት አማራን ሲያሳድዱ፣ ሲጨፈጭፉና ሲያፈናቅሉ እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጣና ዳር ዘና ብለው በአማራ ህዝብ ስቃይ የደስታን ኑሮ ከዚህ በኋላ የሚኖሩ መስሏቸው ከሆነ ተሸውደዋል።
አሁን የአማራ ህዝብ ትግል ከራስ ይጀምራል። ማንኛውንም የወያኔ ጆሮ ጠቢ፣ አቃጣሪ፣ አለቅላቂና አሽቃባጭ አማራን መመንጠር እንጀምራለን። ቤታችን ሳናፀዳ ሌላውን ለማፅዳት መሞከር ብዙ ኪሳራ ስላለው ሆዳቸው ሞልቶ በህዝባችን ሞት በሚያጋሱ የብአዴን ካድሬዎች ላይ ሰይፋችን ይመዘዛል። ብአዴን የአማራ ተወካይ ወይም የትግራይ ተወካይ መሆኑን በግልፅ ያሳይ። ከዚህ በኋላ በአማራ ሞትና ስቃይ እንጀራ እየበሉ ለመኖር የተሰለፉ የብአዴን ካድሬዎች ወዮላቸው። ለወገን ሳይሰሩ በወገን ላብ መኖር ፈፅሞ አይቻልም። ብአዴን ከህወኃት ጋር ያለው ጋብቻ ይፍረስ ወይም ጓዛቸውን ጠቅልለው መቀሌ ይግቡ። የአማራ መሬት ሲነጠቅ፣ ህዝቡ ሲፈናቀል፣ ሲሰደድና ሲገደል እያዬ የተኛ መሪ ስለ አማራ ለማውራት የስነ ምግባርም ሆነ የሞራል ብቃት የለውም። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ማንነታቸው የሚለካበት ወሳኝ የታሪክ ዘመን ጋር ተፋጠዋል። ምርጫቸውም ሁለት ብቻ ነው። ስልጣን፣ ክብር፣ ዝና፣ ደስታ ይቅርብኝ ብለው እንደ ሙሴ ከህዝባቸው ጋር መከራን ለመቀበል መምረጥ ወይም ስልጣን፣ ብርና ክብር ይበልጥብኛል ብለው ከወያኔ ጋር በማበር ህዝባቸውን መጨፍጨፍ።
የአማራ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ አዴሃን/ የብአዴንን አስቸኳይ ውሳኔ ይፈልጋል። በአምስት ቀናት ውስጥ ብአዴን በወልቃይት፣ ዳንሻና ሌሎችም የአማራ መሬቶች ላይ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን የወያኔ ፋሽስታዊ ጭፍጨፋ በማውገዝ ከህዝብ ጎን በመቆም ወያኔን በቃ በማለት የአቋም መግለጫ ካላወጣ አዴሃን የአማራን ህዝብ እየደረሰበት ካለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመታደግ አሁን እያደረገ ካለው ትግል በላይ አድማሱን አስፍቶ የዘረኞችን ሰንሰለት በመበጣጠስ አኩሪ ታሪክ ሊሰራ ተዘጋጅቷል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ወኔውም፣ አቅሙም አለን።
በመሆኑም አዴሃን የአማራን ህዝብ ከጭፍጨፋ ለመታደግ መላው የአማራ ህዝብና ሌሎችም የአገራችን ህዝቦች በስርዓቱ ላይ በጋራ እንዲነሱ አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል። ከዚህ በላይ ትዕግስት፣ ከዚህ በላይ መከራ፣ ከዚህ በላይ ስደትና ሞት አያስፈልግም። ወያኔን በቃ ብለህ ህዝባችን ተነስ። አማራው በያለህበት በመደራጀት በወያኔ ሎሌዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምር። አዴሃን ትናንትም፣ ዛሬም ወደፊትም ለህዝባችን አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ይገኛል። ህዝባችን በያለበት አዴሃንን በመቀላቀል የነፃነት ትግሉን ታቀጣጥል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለመላው የአገራችን ህዝቦች!!!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s