“ተማሪዎችና መምሕራን ታስረው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል” የመንዲ ከተማ ነዋሪዎች – ጃለኔ ገመዳ, ጽዮን ግርማ (VOA)

258F6B9C-EE3D-4C9C-8681-7A26585F6EC5_w640_r1_s_cx0_cy24_cw0

በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ መምሕራንና ተማሪዎች ታሥረው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን እንዲሁም ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን በከተማው ውስጥ የሚገኝ የገበያ ቦታ መቃጠሉን በዚህ ቃጠሎም የመንግሥት እጅ አለበት የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

አቶ ኩመላ ኬና የተባሉ የመንዲ ከተማ ነዋሪ ስለ ሁኔታው ሲናገሩ፤ ሰኞ መጋቢት12 ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ የሚወስደው መንገድ አምስት ቦታ  ዘግተዋል ያሏቸውን ሰዎችለመያዝ የከተማውና የፌደራል ፖሊሶች ከተማ ውስጥ ገብተው፤ ዐሥራ ሰባት መምሕራንናተማሪዎችን አሥረው ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዳቸውን፣ እንዲሁም ማክሰኞ መጋቢት 13ቀን  በከተማው ውስጥ የሚገኝ የገበያ ቦታ መቃጠሉን፣ በዚህ ቃጠሎም የመንግሥት እጅአለበት የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።ይህን በተመለከት የአካባቢው ፖሊስ ምንም የማውቀው ነገር የለም ሲል የከተማው ከንቲባበበኩላቸው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ሰዎች እንደተለቀቁ ገለፀዋል።የገበያ ቦታውመቃጠሉን አምነውም ማጣራት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የኦሮመኛ ዝግጅት ከፍል ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማታቀርበዋለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s