“ኢትዮጵያ እና ክርስቲያን ልጆቿ ባይኖሩ ኖሮ የእስልምና ሃይማኖት በለጋነቱ ይጠፋ ነበር” ግብጻዊው ኢማም ሺክ አልታይብ ሰሞኑን ከሰጡት አስተምሮት የተወሰደ

muslim

ከታምሩ ገዳ

 

አገራችን ኢትዮጵያ በ አሁኑ ወቅት በአለማችን ላይ በርካታ ተከታዮች ካሏቸው የእምነት ተቋማት መካከል አንዱ ለሆነው እና ከ1.6 ቢሊዮን በላይ አማኞች እንዳሉት ለሚገመተው ለእሰልምና ሃይማኖት የክፉ ቀን ደራሽ እና ባለወለታ አገር መሆኑዋን የአመነቱ ተከታይ ኣና ሰባኪ የሆኑት አንድ ታዋቂ ኢማም ሰሞኑን ለምራባዊያን የፓርላማ አባላት/የሕዝብ እንደራሲዎች በግንባር ተገኝተው የምስክረነት ቃላቸውን ሰጡ።


ይህንን ታላቅ ታሪካዊ ኣና ሃይማኖታዊ የእማኝነት ቃላቸውን ያሰሙት በግብጽ የታልቁ የ አል- አዛር መስጊድ ኢማኣም የሆኑት ታዋቂው ሺክ አህመድ አልታይብ ሲሆኑ ታላቁ ኢማም ባለፈው ሳምንት ከጀርመን የፓርላማ አባላት/የሕዝብ እንደራሲዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት በሃይማኖቶች መካከል ሊኖር ሰለሚገባው መቻቻል እና የዘመኑን የአሸባሪነትን አባዜ እንዲት መዋጋት እንደሚቻል ( ኢንተርፊዝስ ዲያሎግ ኢንድ ኮምባቲንግ ቴረሪዝም ) በሚለው ርእሰ ጉዳይ ላይ ባሰሙት ንግግራቸው “የክርስትና እምነት ለመጀመሪያዎቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች መጠጊያ ነው ። ያለ ኢትዮጵያ (የድሮዋ አቢሲኒያ ) እና በጊዜው መጠጊያ እና ከለላ የሰጡን ደጉ ንጉሷ እርዳታ እና እገዛ የእሰልምና እምነት ገና በእንጭጭነቱ / ሳይስፋፋ ሙሉ በሙሉ የጠፋ ነበር “በማለት ነቢዩ መሀመድ እና ተከታዮቻቸው በጊዜው በመካ መዲና ዙሪያ ከነበሩ ተቃዋሚዎቻቸው ግድያው ፣ በደሉ እና መዋከቡ ሲበረታባቸው ተከታዮቻቸውን “ መከራው እና ችግሩ እስኪያልፍ ድረስ ወደ ኢትዮጵያ/አቢሲኒያ ሂዱ። በዚያ መልካም ንጉስ እና ደግ ሕዝብ ታገኛላችሁ “በማለት ተከታዮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንዲሰደዱ መምከራቸውን የሚገለጸውን ታሪክ እና ሃይማኖታዊ ጠቀስ አሰተምሮታቸውን ለጀርመን የፓርላማ አባላት/የሕዝብ እንደራሲዎች በመግለጽ የእስልምና ሃይማኖት በመጀመሪያ ምን ያህል ችግሮች ገጥመውት እንደነበር ፣ቀደምት ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖችም ለሙስሊም ወገኖቻቸው ምን ያህል ባለወለታዎች/ እንግዶችን እና የተቸገሩትን ተቀባዮች እነደ ነበሩ እና ሁለቱ እምነቶችም ምን ያህል ታሪካዊ እና ተደጋጋፊዎች መሆናቸውን እሰረግጠው መናገራቸውን ታዋቂው አሃራም ጋዜጣ በመጋቢት 16/ 2016 እኤ አ እትሙ እስነብቧል።


ይህ የታዋቂው ኢማም አባባል በዙዎች የአለማችን እድሜ ጠገብ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደርን ተግብረናል / እንተገብራለን የሚሉት አገሮች በአሁኑ ወቅት በ ተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የመቻቻል እና የፍቅርን ዘርን መዝራት ተስኗቸው በምትኩ ትልቅ የጥላቻ እና የልዩነት ግንብን በመገንባት የሚያድረጉት ፍጹም ደካማ የሆነው የእራስ ወዳድነት ፍልስፍናቸው እንደማይሰራ እና እንዳልሰራም ፣ ነገር ግን መልካም አስተዳደር እና ዴሞክራሲያዊ መንግስት እና በሕዝብ የተመረጠ መሪ እሰከ አሁን ድርስ የሌላት ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ ግን በህገ ልቦናቸው (በውስጣቸው ) ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት እኩል ናቸው የሚለውን ተፈጥሮአዊ እና ሃይማኖታዊ አስተሳሰብን እንዴት መተገበር እደሚቻል የኢትዮጵያዊያን የመልካም ጉርብትና እና ተቻችሎ የመኖር ታሪክ በጥሩ ምሳሌነቱ እንዲጠቀስ አስችሎታል ።


ሺክ አህመድ አልታይብ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከፓርላማ አባላቱ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች እና አሰተያየቶች መልስ ሰጠተዋል። ለምሳሌ ያህል የዘመን አመጣሹ የአክራሪ ሙስሊሞች እንቀሰቃሴን በተመለከተ ሺክ አህመድ ሲመልሱ “በዚህ ዘመን አመጣሹ ወረርሺኝ/አክራሪነት ዋንኛ ተጠቂዎቹ ሙስሊሞች ናቸው ።አክራሪነትን ለማሸነፍ ከተፈለገ ብቸኛው መንገድ በምእራቡ እና በምስራቁ አለም በሃይማኖትች መካከል መቻቻልን መፈጠር ፣ በአማኞች መካከልም ቢሆን ግልጽነት እንዲሰፍን ማድረግ፣ ውጥረቶችን እና ግጭቶችን በቀላሉ ያሰወግዳል”ብለዋል። ከዚህ አኳያ የጀርመን መንግስት በተለይ ቻንሰለር አንጃላ ማርከር በእርስ በርስ ጦርነቶች አገራችውን እና ቀያቸውን ጥለው ወደ አወሮፓ የተሰደዱ የመካከላኛው ምስራቅ ሰደተኖችን ያለ አድሎ መቀበላቸውን አመስገነዋል። እርምጃውንም በአድናቆት ተመልክተውታል። የምእራቡን ዲሞክራሲያዊ ስርአትን ወደ መካከላኛው ምስራቅ ለማስረጽ የሚደረገውን ሙከራ በተመለከተ ሲናገሩ” ዲሞክራሲ የአንድ ቀን ግባት ሳይሆን የባህል ለውጥን በማጎልበት፣ብርቱ ውይይት እና ምክክር ማድረግ፣ ትምህርት፣ የንግድ ልውውጥን እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማድረግ የዲሞክራሲ ስርአትን በሂደት ማጎልበት ያቻላል።” ብለዋል።


ባለፈው እሁድ ወደ ጀርመን በማቀናት ከተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ፣ ከፓርላም አባለት እና ከፖለቲከኞች ጋር ምክክር ያደረጉት ታዋቂው ግብጻዊው የሱኒ ሙስሊም የሃይማኖት አባት የሆኑት ሺክ አህመድ አልታይብ አኤአ ከ 2010 ጀምሮ ስልጥናቸውን ያገኙ ሲሆን ከ 80 ሚሊዮን በላይ በሚገመቱ ግብጻዊያን ሙስሊም ተከታዮቻቸው ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነት እና ታላቅ ሃይማኖታዊ ስልጣን ያላቸው ፣የ ታላቁ የ አላዛር መስጊድ እና ዩኒቨርሲቲ የበላይ ጠባቂ ሲሆኑ እኤ አ በግብጽ /አለክሳንደሪያ ውስጥ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እና ህንጻ ቤተክርስቲያናቸው በአሸባሪዎች ጥቃት ሲድርሰበት በወቅቱ ካቶሊካዊቷ ቫቲካን ድርጊቱን በ ጽኑ በመቃውም ያሰማቸውን ጸረ እስልምና አስተያየትን ተከትሎ በካይሮ እና በቫቲካን መካከል የተቀዛቀዘውን ግንኙነትን ዳግም በማደስ ረገድ የመጀመሪያው ግብጻዊ የሃይማኖት አባት እንደሆኑ እና በወቅቱም በግብጽ ክርስቲያኖች ( የኦርቶዶክስ አምነት ተከታዮች )ላይ በደረሰው አደጋ ለብጹ ቲወድሮስ ሁለተኛው በግንባር በመገኘት ለእርሳቸው እና ለምእመናኑ ሃዘናቸውን በመግለጽ እና የሽብር ተግባሩንም በጽኑ በማውገዝ ሃይማኖታዊ እና ሰበ አዊ ተልኳቸውን የተወጡ አባት መሆናቸው ታውቋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s