ሠማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። የሚባረሩ ፖለቲከኞች ተለይተው ታውቀዋል (ኤርሚያስ ቶኩማ‬)

ሠማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። የሚባረሩ ፖለቲከኞች ተለይተው ታውቀዋል (ኤርሚያስ ቶኩማ‬)

ሠማያዊ ፓርቲ በሃገራችን ሠላማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ተስፋ ከተጣለባቸው ፓርቲዎች ውስጥ በእድሜ አጭር ቢሆንም በውስጡ በያዛቸው ጠንካራ አባላቱ የተነሳ ለአመታት ተኝቶ የነበረውን የሰላማዊ ትግል ከሞተበት አንስቶ መልካም የሚባል በወሬ ሣይሆን በተግባር የተደገፈ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እያካሄደ ያለ ፓርቲ ነው ::

በዚህ እንቅስቃሴ የተነሳ የፓርቲው አባል የሆነው ሳሙኤል አወቀ ተግድሏል፤ የኢንጂነር ይልቃል እጅ ተሰብሯል፤ የሺዋስ፣ ዮናታን፣ ማቲያስ እና በርካቶች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፤ ወረታው ከስራው ተባሯል፤ ወይንሸት ጭንቅላቷ ላይ የመሰንጠቅ አደጋ አጋጥሟታል፤ በርካቶች በድብደባ ምክንያት ሕመምተኛ ሆነዋል፤ ጌታቸው ሽፈራው የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጣ ላይ ትፅፋለህ ተብሎ ታስሯል ይህ ሁሉ ምንም ማለት አይደለም አንድ ታጋይ ትግል ውስጥ ሲገባ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የደረሰባቸው ጉዳቶች ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ እሙን ነው ሆኖም አምነሀቸው አብረህ ትግል ውስጥ ያሉ ጓዶችህ ለኢህአዴግ አድረው ፓርቲህን ሲያፈርሱት ስታይ ያማል።


ነገሩ እንዲህ ነው ኢህአዴግ ሠማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ የፓርቲው አባላትን መጠቀሚያ ለማድረግ ሲሯሯጥ መቆየቱ አይዘነጋም ታድያ ነገሮች ተመቻችተው ከሰሞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲተሮች የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃልን ጨምሮ ወረታው፣ ወይንሸትን እና ስለሺን በገንዘብ ማጭበርበር በመክሰስ ከፓርቲው ለማገድ ውስጥ ለውስጥ ተስማምተው የጨረሱ ሲሆን የኢዲተሮቹን ውሣኔ እሁድ ይፋ የሚያወጡት ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጠቅላላ ጉባኤው የተጠቀሱትን አመራሮች ለማባረር ውስጥ ለውስጥ እየተሠራ ይገኛል የሚገርመው ኦዲተሮቹ ያሳለፍነው እሁድ ከሁለት የገዢው ፓርቲዎች የደህንነት ሐይሎች ጋር በመሆን እነይልቃልን እንዴት ማባረር እንዳለባቸው ተስማምተው ጨርሰዋል።

እነዚህ ሰዎች ከዚህ ቀደም ጠንካሮቹን ዮናታን፣ እያስፔድንና ዮናስን ከፓርቲው ማባረራቸው አይረሳም። እኔ በግሌ ሠማያዊ ፓርቲን የማውቀው አሁን ይባረራሉ በተባሉት ሀገር ወዳድ ግለሰቦች እና በተባረሩት ወጣቶች ምክንያት ነው። እነዚህ ድንቅ ወጣቶች ሰማያዊ ውስጥ ባይኖሩ ሰማያዊ ፓርቲ በሕይወት መኖሩንም እኔንጃ ስለሆነም ሁላችንም በሰላማዊ ትግል ኢህአዴግን በማስወገድ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት እንችላለን ብለን የምናስብ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከእነኢንጂነር ይልቃል ጎን በመቆም ሰማያዊ ፓርቲን ከመፍረስ እናድነው።
በቀጣይ ሰማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ እየሰሩ ያሉ ግለሰቦችን ማንነት ከመረጃ ጋር የማቀርብ መሆኔን ከወዲሁ እገልፃለሁ።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s