በአዲስ አበባና በዙሪያዋ መሬቶችን በእጅ አዙር ለመግዛት ሕወሓት ደላሎችን ሊያሰማራ ነው::

ሕወሓት ስልጣኑን እና ጠበንጃን መከታ በማድረግ ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ አከባቢዎች ገበሬዎችን በማፈናቀል እጅግ በርካታ ዜጎችን ለችግር የዳረገ ሲሁን ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ዙሪያ በግብርና የሚተዳደሩ ነባር ነዋሪዎችን በሕግ እና ደንብ ሽፋን ማስተር ፕላን በማውጣት ለማፈናቀል ሲዘምት በደረሰበት ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ማስተር ፕላኑን እስከመሰረዝ ደርሷል::ሆኖም በእጅ አዙር ገበሬውን በተለያዩ ጥቅሞች በማታለል ደላሎችን አሰማርቶ ከውጪ አገር ባስመጣቸው የሕወሓት አባላት ስም መሬቶችን በመግዛት ለሪል ስቴት ሊያውላቸው መሆኑ ከነደፈው እቅድ ተገኝቷል::

Minilik Salsawi's photo.

ሕወሓት በአዲስ አበባ በተለይ በኦሮሚያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ የበላይነቱን ይዞ ሕዝብን እየገዛ እና እያስደነገጠ ለመኖር እየገደለ እና እያሰረ ስልጣኑን ለማስረዘም ከሚፈነቅላቸው ድንጋዮች አንዱ የትግራይ ተወላጅ የሆኑአ በውጪ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እያሰባሰበ በማምጣት አስፈላጊውን የመንግስት ገንዘብ ፈሰስ በማድረግ በኢንቨስትመት ስም ከፍተኛ የሆነ የመሬት ቅርሚያ አድርጎ የመሃል አገር ለዋሪ ሕዝብን ገፍቶ በማውጣት የከተማ ታሪኮችን በማጥፋት የራሱን ልእለ ሃያል የኢኮኖሚ የበላይነት የመገንባት እቅዱን ውስጥ ውስጡን እየገፋበት ይገኛል::ሲሉ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ሰብስቦ ያመጣቸውን ካድሬዎቹን ነባር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመኖሪያ ቤት እጦት እየተቸገሩ ለካድሬዎቹ ግን በነፍስ ወከፍ ለአንድ ግለሰብ 3 እና 4 ኮንዶምኒየም ቤቶቹን በማደል ሕዝብ በችግር ተቆራምዶ በገዛ አገሩ ላይ ባይተዋር እንዲሆን አድርጎታል::

ለሕወሓት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በሚገኙ አከባቢዎች የገበሬውን መሬት በአፈ ጮማ ደላሎች አስማምቶ ለመግዛት የእጅ አዙር እንቅስቃሴ የጀመረው ሕወሓት ደላሎቹ ገበሬዎቹን በተመለከተ አስፈላጊ ጥናት እንዲያደርጉ እና መረጃ እንዲሰበስቡ ለማድረግ ወደ ስራ የገባ ሲሆን አዘናግቶ ከሚያጠቃው ሕወሓት መሰሪነቱን የማያውቁ ምስኪን ግበሬዎች እንዳይታለሉ ሲሉ ለምኒሊክ ሳልሳዊ መረጃውን የላኩ ምንጮች ተናግረዋል

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s