“አማራ ሽንታም ነው፥ አማራን እንዳያንሰራራ አድርገን እንቀብረዋለን” – ሰብለወንጌል ዘአማራ

Amhara Democratic Movement Force - Ethiopia 2

ትናንት አቶ ዘመነ ምህረትን በአማራነቱ ላይ ወያኔዎች ተሳለቁበት (ምንም እንኳ አማራነት የሚያኮራ እንጅ እንደወያኔዎች ያሚያሳፍር ታሪክና ማንነት ባይኖረውም)። አቶ ዘመኔ ካሴ አማራ በመሆኑ ብቻ የነታማኝ በየነ ዘር፣ የነአበበ ገላው ዘር፣ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ዘር እያሉ የሰው ልጅ ላይ ሊደርስ የማይገባውን ግፍ ሰሩበት። ትናንት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ውስጥ ሲሰራ የነበርው አቶ ዘመነ ምህረት “እስር ቤቱ በሙሉ ከ90% በላይ እስረኛው አማራ ነው። አማራነትን ለማጥፋት ወያኔዎች ታጥቀው ተነስተው ላለፉት 42 አመታት እየተገበሩት ነው። አማራነት ወንጀል ሁኗል” አለን። እሱም ፊቱን አማራን ወደማዳን እንደሚያዞር ንግግሩ ይጠቁማል። ወያኔዎች ማድረግ የሚችሉትን ግፍ ሁሉ በአማራ ላይ እያደረሱ ይገኛሉ። አማራው ግን አሁንም ተኝቷል። አማራው ተኝቷል ስል በጎንደርና በተለያየ አካባቢዎች እየታገሉ ያሉ ጀግኖችን አይጨምርም። አማራው ተኝቷል ስል ምንም መረጃ የሌለውን ምስኪኑን አርሶ አደር አይጨምርም (ይህ አርሶ አደር የመረጃ ክፍተት ስላለበት ሊወቀስ አይገባውምና)። አማራው ተኝቷል ስል በማህበራዊ ሚዲያውና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ድምጻቸውን ስለአማራ ሲሉ ከፍ አድርገው የሚጮሁትን አያካትትም። አማራው ተኝቷል ስል ግን እውቀት እያላቸው፣ መረጃው እያላቸው፣ ማድረግ የሚችሉት ነገር እያላቸው አማራን ሳያግዙ የተኙትንና አንዳንዶች ይባስ ብሎ ስለአማራ የሚታገሉትን ወገኖቻችንን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለማሸማቀቅ ጥረት የሚያደርጉትን ነው።
================
ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የመጀመሪያው የልብ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው። ነገር ግን አማራ እየጠፋ ሳይ ዝም አልልም አሉ። ንብረትህ በእሳት እየወደመ የእሳት አደጋ ሰራተኛ አይደለሁምና እሳቱን አላጠፋም ብለህ አትቅመጥም፥ እኔም ፖለቲከኛ አይደለሁም ነገር ግን በአማራው ወገኔ ላይ የሚደርሰው ግፍ ዝም ብየ እንድቀመጥ አያደርገኝም። ስለአማራ እጮሃለው፣ ስለአማራ እታገላለው፣ ስለአማራ ህይወቴን እሰጣለው አሉ። ስለአማራም ህይወታቸውን ሰጡ። ወያኔ በእስር ቤት አንገላቶ ገደላቸው። ዛሬም በየእስር ቤቱ አማራዎች እየታደኑ ይሰቃያሉ። አማራ ሁነህ ንብረት አታፈራም፣ ነግደህ አታተርፍም፣ ተናግረህ ቤትህ በሰላም አትቀመጥም። የመላ ኢትዮጵያ እስር ቤት በአማራ የሲቃ ድምጽ ተውጣለች። ሰዎች ስለኢትዮጵያ ይጮሃሉ፣ ግን ስለአማራነታቸው ይገረፋሉ፣ ይገደላሉ፣ ይሰደዳሉ። ስለዚህ መስዋዕትነቱን ስለአማራ ስንል ለምን አንቀበለውም? እንደፕሮፌሰር አስራት ለምን ስለአማራ ስንል አንሞትም? ለምን ስለአኢትዮጵያ እያሰብን በአማራነታችን ሱሪያችንን አውልቀን እንገረፋለን። አማራ ሽንታም ለምንስ እንባላለን። ይህን ስል እንባየ ባይኔ ግጥም ብሎ ነው የጻፍኩት። የሃዘን እንባ ግን አይደለም። የተጠቂነት እንባ ነው። የእልህ እንባ ነው፣ ደግሞም የንዴት እንባ ነው። በእናንት ስለአማራ የሚጮህ ጩኸት ጆሯቹህ ላይ ሰለማይደርሰው አማራዎች ስል በንዴት አልቅሻለው። አማራ ሽንታም (ቃሉ ምን ያህል እንደሚቀፍ አያቹህት አይደል) ነው እየተባሉ ግዜ ባነሳቸው ወያኔዎች እስር ቤት ውስጥ ስንት በደል እነደደረሰባቸው ና እየደረሰባቸው እንደሆነ የታወቀ ነገር ነው።
===============
አማራ መሬቱን ተቀምቷል፣ ስብዓአዊነቱን አጥቷል፣ እንደእንስሳ ታርዶ ተበልቷል፣ እንደእንስሳ ቆዳው ተገፏል፣ በገደል እስከነፍሱ ተጥሏል፣ በጅምላም በነጠላም ተገሏል፣ በኤች አይቪ ባይረስ ተመርዟል፣ማምከኛ መድፌ ተወግቷል….ግን አሁንም ስለ አማራነት የሚጮህ የለም። ይህን ሁሉ ግፍ የምታቁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያላቹህ አማራዎች እንኳ ስለአማራነት ልዩነትን አቻችሎ ከመታገል ይልቅ ትናንትም ዛሬም ነገም ትናቆራላቹህ። የአማራን በደል የምታቁ ግለሶች በሙሉ ለአማራ ችግር ጆሮ ዳባ ልበስ ብላቹህ ሃገሬ ሃገሬ ትላላቹህ። ነገ በወያኔ እጅ የገባቹህ ቀን ግን ስለአማራነታቹህ እንጅ ስቃዩን የምትቀመሱት ስለኢትዮጵያዊነታቹህ አይደለም።
አማራ የሆናቹህ ፕሮፌሰሮች፣ ዶክተሮች፣ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ስለአማራ በደል ማውራት አቁማቹሃል። የወያኔ በደል በሁሉም ህዝብ ላይ ቢሆንም ቅሉ አማራን ነጥሎ እንደሚያጠቃ እያወቃቹህ ዛሬም ወይ ዝም ብላቹሃል፣ ወይ ስለአንድነት ትዘምራላቹህ፣ ወይም ስለአማራ በአቅማቸው የሚለፉትን ጠልፋቹህ ለመጣል ትታትራላቹህ። ይህ ስህተት ልንመልሰው የማንችለው መስዋዕትነት እያስከፈለን እንደሆነ እሙን ነው። ጠላታችን ሌት ተቀን አይተኛም። እኛ ግን ሌቱንም ቀኑንም ተኝተናል። ስለዚህም ነገ ሮማ እንደሚባሉት ጅፕሲዎች ተበታትነን እንጠፋለን። ሃገር፣ ቀየ ሳይኖረን ከሰው በታች ሁነን እንኖራለን። የያዛቹህት እውቀትና የወያኔ የ42 አመታትና በላይ ስራ ይህንን እንድትገምቱ ያስችላቹሃል። ግን አማራን ለማዳን ስትንቀሳቀሱ አናይም።
============
የወያኔ መውደቅ ለሁሉም ህዝብ መፍትሄ ያመጣል፥ ለአማራም መብትና ጥቅም መከበር የወያኔ መውደቅ ትልቅ ሚና ይጫዎታል ስለዚህ ለአማራ ከመታገል ይልቅ በአንድነት ወያኔን ለመጣል መታገል ይሻላል ብላቹህ ሊሆን ይችላል። አዎ የወያኔ መውደቅ ለአማራ ጥሩ ዕረፍት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አማራ በትግሬ፣ በኦሮሞ፣ በቤንሻንጉል፣ በሱማሌ፣ በጋንቤላ፣ ደቡብ ውስጥ ባሉ አንዳንድ ህዝቦች ዘንድ እንዲጠላ ተደርጓል። ስለዚህ የአማራ ችግር በወያኔ መውደቅ ብቻ የሚያከትም አይደለም። ከዛም በላይ ነው። ዛሬ ያንቀላፋቹህ፥ ዛሬ ስለአማራ የሚጮሁትን ለመጥለፍ የምትኳትኑ ሁሉ ነገ ታሪክም ህሌናቹህም ይወቅሳቹሃልና ስለህዝባቹህ ስትሉ ድምጻቹህን አሰሙ።
===============
ሰሞኑን እንኳ ወልቃይቶች የሚደርስባቸው ወከባ ምንም ድምጽ አላገኘም። ሙህራኖችና ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች ጸጥ ብለዋል። አንዳንዶች ስለሰብዓዊነት ይሰብካሉ፥ ነገር ግን አማራ ላይ የሚደርሰው ኢ-ሰብዓዊ ጭካኔ አታያቸውም። ወያኔ የአማራ ህዝብ በሰላም እንዳይኖር መሳሪያ በገፍ ወደአማራ ክልል እያስገባ በቅማንት ህዝብ ስም የፈለገውን ያደርጋል፥ እኛ አማራዎች ግን ስለኦሞ ወንዝ አካባቢ የመሬት ቅርምት እንዘምራለን። የአማራ መሬት ለትግራይ፣ ለሱዳን፣ ለቤንሻንጉል ወዘተ ይሰጣል፥ እናንት አማራዎች ግን ለአላህሙዲ ይህን ያህል መሬት በጋንቤላ ተሰጠ ትሉናላቹህ። ወያኔ አማራነትን ለማጥፋት ከሙህራኖቹ ጋር፣ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር፣ ከፖሊስ ሰራዊቱ ጋር፣ ከተራው ህዝብ ጋር፣ ከተማሪው ጋር፣ ከፌደራል እስከቀበሌ ባለስልጣናት ጋር ይዶልታል፥ ተግባራዊም ያደርጋል። የአማራ ሙህራን፣ የአማራ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የአማራ ጋዜጠኞች፣ የአማራ ፖለቲከኞች ግን ምንም ደንታ የላቹህም። ይሄ ዝምታቹህ ነገ ዋጋ እንደሚያስከፍላቹ የታወቀ ነው። ነገ ልትመልሱት የማትችሉት የህሌናና የትውልድ ጥያቄ ይዞባቹህ እንደሚመጣ የታወቀ ነው። ለምሳሌ ዛሬ አማራ ነኝ ለማለት ያልደፈረው የጎጃም አማራው ኢንጂንየር ይልቃል ጌትነት በአማራነቱ በወያኔ ደባ ከመሰረተውና እዚህ ደረጃ ላይ ካደረሰው ሰማያዊ ፓርቲ እንዲፈናቀል ተደርጓል። ነገር ግን ትናንት ኢትዮጵያዊ ነኝ እንጂ አማራ ነኝ አልልም ብለሃል፣ ስለአኢትዮጵያ ታግለሃል ብሎ ማንም አልተወውም። አማራ ነኝ ብሎ የአማራነት ጽዋን አጎናጽፈውታል። አማራነቱ መስዋዕትነት አስከፈለው። ለዚህ መስዋዕትነት ላስከፈልው ማንነቱ ደግሞ ቀድሞ ሊታገልለት በተገባው ነበር። ግን አልሆነም። አቶ ዘመነ ምህረትምም እንዲሁ። መኢአድ ውስጥ ገባና ለኢትዮጵያ ታገለ። ግን ስለአማራነቱ መስዋዕትነት ከፈለ። አሁን አማራነትን ለማዳን መስራት እንዳለበት አመኗል። ስለዚህ እናንተም ስለማንነታቹህ ትታገሉ ዘንድ፣ ስለአማራነታቹህ ትቆሙ ዘንድ፣ ስለአማራነታቹህ መስዋዕትነት ትከፍሉ ዘንድ ሳይረፍድ ተነሱ።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s