አዲስ አበባ በድጋሚ በታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ልትመታ ነው

ከወር በፊት አዲሱን የአሽከርካሪዎች ህግ በመቃወም የታክሲ ሹፌሮች ለተከታታይ ሁለት የሥራ ቀናት አገልግሎት በማቆም አድማ መምታታቸውና መንግስትም ከአድማው 12 ሰዓታት ቀደም ብሎ አዲሱን የአሽከርካሪዎች ደንብ ለሶስት ወራት በስራ ላይ ከማዋል እንደሚቆጠብ መግለጹ አይዘነጋም፡፡

በመንገድና ትራንስፖርት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በኩል ለሶስት ወራት ስራ ላይ እንደማይውልና ውይይት እንደሚደረግበት የተነገረለት ደንብ አሁን ያለምንም ውይይትና ማሻሻያ  በተጠናከረ ሁኔታ በሥራ ላይ እየዋለ በመሆኑ አሽከርካሪዎቹ ያቋረጡትን የስራ ማቆም አድማ ለመቀጠል መወሰናቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል።

የተወሰኑ ሹፌሮች በአዲሱ ደንብ መሰረት መንጃ ፍቃዳቸውን ተቀምተው ሥራቸውን ለማቆም መገደዳቸውን የተመለከቱ አጋሮቻው ለመጋቢት 19 እና 20 በድጋሚ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ውስጥ ለውስጥ ተነጋግረው መወሰናቸው ታውቋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s