እየተጠራ የሚገኘው የኢንተርሀሙዌ የእልቂት ዘመቻ ይቁም

 

Asgede

ኢንተርሀሙዌ የሚል ቃል በ1997  ጠ /ም መለስ በወቅቱ የነበሩ ተወዳዳሪ የፖለቲካ  ፓርቲዎች  ሲበረቱበት እንዳያሸንፉት ስለሰጋ  ተጨንቆ ተቃዋሚዎቹን ለማፈንና ለመምታት እንዲመቸው ፈጽሞ በመሬት የሌለ  ወይም ያልነበረ ን ነገር  ለግዜው የፖለቲካ ፍጆታ ሲል  ተቃዋሚዎች  እንደ ሩዋንዳው ታጣቂ ቡድን ኢንተርሀሙዌ የዘረኝነት   ጥቃት ሊፈጽሙብን ነው በማለት መጥፎ ስም ለጥፎባቸው እንደነበር ማናችንም አንዘነጋውም፡፡

በዚያ  ምርጫ ተቃዋሚዎች  ካሸነፉ በኋላ ሽንፈቱን ላለመቀበል  የሁሉም ተወዳዳሪ ፖለቲካ ፖርቲዎች መሪዎችና አባላቶቻቸው ፣ ደጋፊዎቻቸዎ በቃሊቲ ፣በዝዋይ ፣ ሸዋ ሮቢት፣  በጦላይ፣ በታጠቅ ጦር ሠፈር፣ በብር ሸለቆና  በሌሎች በደርዘን  በሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች እንደ እንስሳ በጨለማ ቤት ታጎሩ::

ብዛት ያላቸው ዜጎች የገቡበት  ሳይታወቅ ደብዛቸው ጠፍቶ ቀሩ:: እነዚህ ዜጎች ግን የታሠሩት፣ የተሰቃዩትና የጠፉት የኢንተርሀሙዌ  ወንጀል ተገኝቶባቸው ሳይሆን ራሳቸውን ለመለስ ቡዱኖች  የስልጣን  እድሜ ማሳጠሪያ በማድረግ በማቅረባቸው ነበር::

የተከበራችሁ ወገኖች ያ ወቅት በግሌ በመቀሌ ከተማ ከህወሓት ኢህአዴግ  ለተወካዮች ምክርቤት ፓርላማው ፊት ለፊት በሰላማዊ መንገድ የተፋለምኩበት  ነበር:: በግዜውም የኢንተርሀሙዌ ቅጥረኛ ተብዬ ነበር ::ህወሓት መጥፎ ስም በመለጠፍ  ልምድ የተካነ ነበርና ብዙም አልገረመኝም ::

ያሁኑ ይባስ

የብአዴንና የህወሓት አመራሮች  በደመቀ መኮንን ፣በአባይ ወልዱና ገዱ አንዳርጋቸው ቅጥረኛ ተላላኪ ካድሬዎች  በየፊናቸው  የኢንተርሀሙዌዎችን  መርህ በመከተል  የአማራና የትግራይ ህዝብን  በማያውቁት ህቡዕ  አጀንዳ በመቀስቀስ  ወደ ከፋ የዘረኝነት እልቂት እየነዱት መሆኑን  እንመለከታለን ::  ይህ አደገኛ የኢንተርሀሙዌ  የእልቂት አደጋ  እንዲፋፋም ሁለቱ ዘረኛ ቡዱኖች ሁለቱን ሰላማዊ ህዝብ የዘረኝነት እልቂት እንዲፈጽም ፊት ለፊት አፋጥተው ይገኛሉ::

ካለፉት ሁለት ቀናቶች  ጀምረውም  ገዱ አንዳርጋቸው ያሰማራቸው  ትግራይ ነን  ወደሚሉት ገበሬዎች ሰርገው በመግባት እንስሳትንና ንብረት እንዲዘርፉ በማድረግ  ወንጀል መፈጸም ጀምረዋል :: በተጨማሪም ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ    ይሰወራሉ ፡፡

በሌላ በኩል የአባይ ወልዱ ቡድንም አማራ ነን ወደሚሉት አስርገው በማስገባት ሰዎችን እንደሚጠልፉ፣እንደሚሰውሩ፣ እንስሳትንና ንብረት እየዘረፉ እንደሚወስዱ  ከአማራም ከትግራይም የሚመጡ ዘገባዎች አሉ:: ይህን  መፋጠጥ ሥንመለከት በትግራይ በአማራ በቅማንት የኢንተርሀሙዌ እልቂት  እየተቀጣጠለና እየፈጠነ እንዳለ እንገነዘባለን::

ይህንን አደጋ ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ የሀይማኖት መሪዎችና  የእድሜ ባለጸጋዎች ለመከላከል  እጃቸውን  እንደማስገባት ባዕድ ይመስል ከዳር ሆነው  መመልከታቸው እጅጉን ያሳዝናል :: በተለይ በማይጨው፣በመቀሌ፣ በዓዲ ግራት፣ በሽሬ፣ በአክሱም፣ በጎንደር፣ በድብረ ታቦር፣ በወልድያ፣በደሴ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በባህርዳር  ዩኒቨርስቲ የሚገኙ  በብዙ መቶሺህ የሚቆጠሩ ሙሁራንና ተማሪዎች ሁኔታው ማሳረጊያ እንዳይደረግለት ዘረኝነትን በመጠቀም የኢንተርሀሙዌን እልቂት በሚቀሰቅሱ  የሁለቱ  ፓርቲዎች  ዘረኞች ላይ ተጽእኖ እንደማድረግ ባዕድ ሆነው ዝምታን መርጠው መመልከታቸው  ሳይማር ያስተማራቸውን ወገናቸውን  መካዳቸውን ያመለክታል ::

ከአስገደ ገስላሴ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s