ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አምባሳደሮችን እየተማጻኑ ነው

tewedros

የህወሃቱ አመራር አባልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ለተመድ የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ቦታ ለመወዳደር የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን መንግስታቸውን አሳምነው ድጋፍ እንዲሰጡ ያደርጉላቸው ዘንድ በመማጸን ላይ መሆናቸው ታውቁዋል።
ሰሞኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን አምባሳደሮች መንግስቶቻቸው በምርጫው ድጋፋቸው እንዲሰጡዋቸው ያደርጉላቸው ዘንድ ሲማጸኑ ተሰመቱዋል። አምባሳደሮቹም በዲፕሎማሲ አነጋገር የተቻላቸውን እንደሚያደርጉ ገልጽውላቸዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ በአሁኑ ወቅት መደበኛ ስራቸውን በመተው በመንግስት በጀት በምረጡኝ ቅስቀሳ የኤምባሲዎችን ደጅ እየጠኑ ሲሆነ፣ ዶ/ሩ እኔ ብመረጥ አፍሪካም ጭምር ትጠቀማለች በሚል የቅስቀሳ ዘዴ ድጋፍ እየጠየቁ ሲሆኑ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት የዳይሬክተርነት ቦታ በተለይ እንደአሜሪካና እንግሊዝ ያሉ የሀያላን ሀገራት ደጋፍ ማግኘት ካልቻሉ በስተቀር የማለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው።
በአሁኑ ወቅት የጤና ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እየመሩ ያሉት ዶ/ር ማርጋሬት ቻን በሀገራቸው ሆንግኮንግ የጤና ሚኒስትር ሆነው ከመስራታቸውም በላይ በአለም የጤና ድርጅትና በሌሎችም አለም አቀፍ ድርጅቶች በከፍተኛ ሀላፊነት የሰሩ መሆናቸው ሲመዘን፣ በብቃትም ጭምር ዶ/ር ቴዎድሮስ ለቦታው እንደማይመጥኑ ከወዲሁ አስተያየት እየተሰጠባቸው ነው። ዶ/ሩ በኢትዮጵያ ባለፉት 24 አመታት ለተፈጸሙት የሰባዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ ናቸው በሚል፣ እርሳቸው እንዳይመረጡ በማህበራዊ ሚዲያ ቅስቅሳ ሲደረግ ቆይቶአል።
ዶ/ር ማርጋሬት እ ኤ አ ጁን 30/2017 ሀላፊነታቸው ስለሚያበቃ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ተሰብስቦ በእሳቸው ምትክ አዲስ ዳይሬክተር አወዳድሮ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢሳት ዜና

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s