ፓርላማው በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ላይ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ቡድኖችን አሰማራ

Aba Dula

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች ላይ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለማጣራት፣ 14 የሱፐርቪዥን የክትትል ቡድኖችን ማሰማራቱ ተገለጸ፡፡
የፓርላማው አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቀደም ሲል ከተከናወኑት የሱፐርቪዥን ሥራዎች በተጨማሪ ሦስተኛው የክትትልና ቁጥጥር ሥራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ላይ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዚህ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ላይ የሁለቱም ከተሞች ምክር ቤቶች ያደራጇቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑም ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ አስተዳደር ሥር ባሉ ጥቂት ክፍለ ከተሞች የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ተከናውኖ እንደነበር ያስታወሱት አፈ ጉባዔው፣ እንደ አዲስ የተጀመረው ክትትል የሁለቱንም ከተማ አስተዳደሮች የመልካም አስተዳደር ሁኔታ በሙሉ ገጽታው የሚያሳይ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሮቹ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች የት እንደደረሱ ለማወቅም እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡ አሁን የተጀመረውን መልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ መፈጸም የግለሰብ ፍላጎትን የሚጠይቅ አለመሆኑን የተናገሩት አፈ ጉባዔ አባዱላ፣ በክትትልና ቁጥጥር ቡድኖቹ የሚገኙ ህፀፆች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚቀርቡና ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
በአፈ ጉባዔነት የሚመሩት ፓርላማ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንድ ፓርቲ አስተሳሰብ ብቻ የተሞላበት የሐሳብ ብዝኃነትን የማያስተናግድ ተደርጎ እንደሚቆጠር የተጠየቁት አፈ ጉባዔ አባዱላ፣ ‹‹እንደ ዘንድሮ ዓይነት የፓርላማ ዘመን ያለ አይመስለኝም፤›› ብለዋል፡፡
የፓርላማ አባላቱ ገዢው ፓርቲን ለማብጠልጠልና ለቴሌቪዥን ፍጆታ የሚከራከሩ ሳይሆኑ፣ ከማንኛውም ጊዜ በላይ ፕሮጀክቶች እንዲፈጸሙና ሕዝቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በሙሉ እምነቱ የሚከራከሩ ናቸው ብለዋል፡፡
‹‹ኢሕአዴግ ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ታግሏል፡፡ ነገር ግን የሕዝብ ምርጫ ውጤቱ ይህ ከሆነ ምን ማድረግ ይቻላል?›› ያሉት አፈ ጉባዔ አባዱላ፣ ‹‹በፓርላማ ውስጥ የፖሊሲ ክርክር ሊኖር አይችል ይሆናል እንጂ መቀዛቀዝና መፋዘዝ አይኖርም፤›› ብለዋል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s