በባህር ዳር፣ ወሎና ጎንደር የመምህራን እጥረት ተከሰተ | ተማሪዎች በአስተማሪ እጦት ፈተና ሳይፈተኑ ቀሩ

ፎቶ ከፋይል

ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ ስር እንዲተዳደሩ ተወስኖ በባሀር ዳር ከተማ አስተዳደር ውስጥ የገቡት ጢስ አባይ፣ መሸንቲ፣ ዘጌና ሌሎችም አቅራቢያ ከተሞች በመምህራን እጥረት የተነሳ ተማሪዎች ፈተና ሳይወስዱ መቅረታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከአካባቢው ገለጹ::

በባህርዳር ከተማ ስር ባሉት እነዚህ ከተሞች ውስጥ የመምህራን እጥረት የተከሰተው የሃገሪቱ የትምህርት ሚኒስተር የባህር ዳር ከተማ ትምህርት ቢሮ አስተማሪዎችን ከዝውውር ውጭ በቋሚነት እንዳይቀጥር በማገዱ ነው ተብሏል:: እንደ ምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ እንዲህ ያለው ተመሳሳይ ችግር በደሴና በጎንደር ከተሞች ውስጥም መከሰቱን እና ተማሪዎች በመምህራን እጥረት የተነሳ ፈተና ሳይወስዱ መቅረታቸውና በዚህም የተነሳ በሕይወታቸው ላይ ትልቅ እክል እንደፈጠረባቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት በባህርዳር የተለያዩ ከተሞች ውስጥ በተለይም የማጅ ደብረንግስት፣ ሳሊ ዋርካና የወርቀምላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሂሳብ፣ እንግሊዘኛ፣ አማርኛና ሌሎችንም የትምህርት ዓይነቶች የሚያስተምሯቸው አስተማሪዎች አጥተው ቁጭ ብለዋል:: በነዚህ የትምህርት ክፍለጊዜዎች ወቅት ተማሪዎች ጊዜያቸውን በጨዋታ እንደሚያሳልፉት የደረሰን መረጃ አመልክቷል:: የከተማው ትምህርት ቢሮ አስተማሪዎችን እንዳገኘ ለነዚህ የትምህርት ዓይነቶች የማካካሻ ጊዜ እንደሚሰጥ ቃል የገባ መሆኑን ያስታወቁት ምንጮቻችን እስካሁን ባለመተግበሩ የተማሪዎቹ ጊዜ እየባከነ ነው ተብሏል::

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s