የመሪ ያለህ ! – የኢትዮጵያ የ2008 ህዝባዊ ንቅናቄ ጥሪ | ዜና ትንታኔ

ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ ለዘ-ሐበሻ ጋዜጣ 

የአዲስ አበባ ጉዳይ የተቃውሞ መነሻ 

የሆነው ከመቼ ጀምሮ ነው?

የአዲስ አበባ ጉዳይ አብይ ይፋ የውዝግብ ርዕስ መሆን የጀመረው በ1991 ዓመተ ምህረት በስልጣን ላይ ያለው የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የኦሮሚያ ክልልን መቀመጫ አዳማ ብሎ ሲወስን ነው። በወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች “እንዴት ኦሮሞ ከእርስቱ ተነቅሎ የክልሉ ዋና ከተማ አዳማ ይሔዳል?” ብለው ተቃወሙ በርካታ ተማሪዎች ተደብድበው ታሰሩ። የተቃውሞው አስተባባሪዎች ናቸው የተባሉት 7 ያህል ‘የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ተልዕኮ ፈፃሚ’ የሚለው ዋናው ክስ ላይ ተደርቦ ተከሰሱ።

ADDIS ABABA

የተቃዋሚዎቹ ሕጋዊ ጥያቄ ራሱ ስርዓቱ ያጸደቀው ሕገ መንግስት የሚሰጠው ሕጋዊ መብት ነው። ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ታገኛለች ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል ይላል። ያ ዝርዝር ዛሬም ድረስ በሕግ ያልተወሰነው ሕወሃት እንዳሰበው እንደልቡ እየዘረፈ ለፖለቲካ ጨዋታ ሕገመንግስቱ ውስጥ ያሰፈረው አንቀጽ እንደልብ ስላላሰራው ነው።

 

በጊዜው ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ የተነሳው የያኔው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞን አገዛዙ በመሳሪያ ለመጨፍለቅ አፍታ አልፈጀበትም። የታጠቁ ፌደራል ወታደሮችን ያለ አንዳች ጥያቄ ግቢ ውስጥ አሰማርቶ በጨለማ በተማሪዎች መኝታ ቤት እየገቡ ጭምር ድብደባ ተፈፀመ። የተማሪዎች መኝታ ቤት ኮሪደር በንፁሃን ደም ጨቀየ። በዱላ አናታቸውን የተፈለጡ፣ መጨበጥም ሆነ መራመድ ያልሆነላቸው በርካቶች ለወትሮው ፀጥ ያለው ግቢ በጣእር ድምፅ ተተካ። ከ400 መቶ የሚበልጡ ተማሪዎች የአንድ ዓመት ትምህርት ተቀጡ:: ከዚያ መሐል ተመልሶ ለመማር በቅድመ 1966 አብዮት ተማሪዎች ለአንድ እድል ያገኘው ….. ህዝብ ለአንድ አገር ያለውን ማህበራዊ ጭቆና ተቃውመው በ1962 መሬት ላራሹ ያለው የነ ጥላሁን ግዛው ትውልድ በብሔር በተከፋፈለ አንዱ ሲገደል አንዱ ቆሞ የሚያይበት ዩኒቨርስቲ ሆኖ አረፈው።

 

የኦሮሞ ተማሪዎች ያን የመሰለ ተቃውሞ ሲደረግ ሌላው ተማሪ አድፍጦ ሲያይ በግቢው የመጀመሪያ አይደለም። ከዚያ ከጥቂት ዓመታት በፊት የአማራ አርሶ አደሮች መሬታቸውን ተነጥቀው ገበሬዎች አራት ኪሎ ፓርላማ ተወካዮቻቸውን ልከውም ሲጠፉና አንዳንዶቹም ታፍነው የደረሱበት ሲጠፉ የክልሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰምተው አማራ አማራዎቹ ተለቅመው ተደብድበው ኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተግዘው ታስረው የሚባረረው ተባሮ የተረፉት በጊዜው የከተማው ከንቲባ በነበሩት በአሊ አብዶ ፊርማ የተዘጋጀ የይቅርታ ደብዳቤ ፈርመው ወደ ትምህርት ተመለሱ የተባረሩት ተባረው ቀሩ።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s