የአባይ ግድብ ለአማራ ህዝብ ያለው አንድምታ

የአባይ ግድብ ከተጀመረ እነሆ 5ኛ አመት ሞላው። ከግማሽ በላይም እንደተጠናቀቀ እየተዘገበ ነው። ይህ ግድብ ከግድብነቱ ባለፈ ፖለቲካዊ አንድምታውም የትየለሌ ነው። እኛ አማራዎች በወልቃይት ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራ እንቅልፍ በነሳን ሰአት፤ በቅማንት እና አማራ መካከል እየተቀሰቀሰ ያለው ግጭት በሚያሳስበን ሰአት እንዲሁም የጎንደር መሬታችን ለሱዳን እንዳይሰጥ ቀንም ሌሊትም በምንጮህበት ሰአት አንደኛ ደረጃ ዜጎች ግን እሳቱን በአማራ ፤ በኦሮሚያ እና በደቡብ ለኩሰው እየሞቁ የግድቡን ክብረበአል በድግስ እና በአበል እያደመቁት ነው። አንድ ሃገር እያለን ሁለት አይነት ዜጎች የሆንበት ሁኔታ ነው ያለው። የሆነስ ሆነ እና የአባይ ግድብ እና የአማራ እጣ ፈንታ ምን እና ምን ናቸው የሚለውን ነገር ማየት ወሳኝ ነገር ነው። በአዲስ መስመር ተከተሉኝ።

የትግሬ-ወያኔ ግድብ ግንባታ በሟቹ መለስ ዜናዊ ከተበሰረበት ጀምሮ የአማራ ህዝብ ብቻውን ወደ 1 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ (967 ሚሊዮን ብር) ተገዶ እንዲሰጥ (ምንም እንኳ እነሱ በፍቃደኝነት ለግሶ ነው ቢሉም) እንደተደረገ ከወራት በፊት የወጣ የኢዜአ ዜና ያመለክታል። መቸም የኢትዮጵያ ህዝብ በደንብ እንደሚያውቀው የአማራ ህዝብ ማለት በህዋሃት መንግስት መዋጮች በኩል ከሁሉም በግንባር ቀደምትነት እየተበዘበዘ ከአለማችን ግን ቁጥር አንድ ድሃ እንዲሆን የተደረገ ምስኪን ህዝብ ነው። ይህንን ያልኩት እኔ ሳልሆን አልጀዚራ ነው። https://www.youtube.com/watch?v=pHs8uNuSguw

የአማራ ህዝብ ግብር በመክፈል ‘ሞዴል ተሸላሚ’ ነው፤ በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት (ትውልድ በማምከን) ‘ደረጃ ተሸላሚ’፤ ‘ህገወጥ መሳሪያ’ በማስረከብ (ራሱን እንዳይከላከል) በማድረግም ለሌሎች ክልሎች አርእያ ነው። የመንግስት የውድቀት ፖሊሲዎች መጀመሪያ የሚተገበሩት አማራ ክልል ነው። አማራ ክልል ማለት የትግሬ ወያኔ የቤተ ሙከራ አገልግሎት ከሆነ 25 አመታት አለፉ። የፖሊሲዎች ውድቀት እና ስኬት አማራ ላይ ተሞክሮ ወደ ሌላው እንደሚሸጋገር ሁላችንም አይን እማኞች ነን።

ይህ አልበቃ ብሏቸው ደግሞ በግድብ ሰበብ አሁን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከሁሉም የአማራ ጉሮሮ እየተነጠቀ ለትግሬ- ወያኔ ግድብ እየተሰጠ ነው። 15 ኪሎ የእርዳታ ስንዴ ለማግኘት እንኳ የጎንደር ገበሬዎች የ200 ብር ቦንድ እንዲገዙ መደረጋቸውን እናስታውሳለን። በዚህም የአማራ ህዝብ ለግድቡ ገንዘብ በማሰባሰብ ከሁሉም ክልሎች የተሻለ ደረጃ ላይ መሆኑን ሆዳሙ ደመቀ መኮነን በኩራት ከመናገር አልፎ እንዲህ ሲል ተናግሯል ” የቀድሞው ታላቁ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ የመሰረት ድንጋዩን ሲያስቀምጡ ግድቡ የመላ አገሪቱ ህዝቦች ፕሮጀክት ነው” ። ይሁን እንጂ ጤነኛ አእምሮ ያለው የአማራ ተወላጅ የአባይ ግድብ ማለት የመላ ሃገሪቱ ህዝቦች ፕሮጀክት ሳይሆን በአጭር ጊዜም ይሁን በረጅም ህዋሃት ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የትግራይ ፕሮጀክት መሆኑን መረዳት ይችላል። እንዴት?

ምክንያቶች ሁለት ናቸው፤ ቅድም እንዳልኩት በአጭር እና በረጅም ጊዜ
በአጭሩ ስናየው የአባይ ግድብ ማለት የሚገነባው በጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን እና በህዋሃት ኩባንያዎች ነው። ከ150 ሚሊዮን ኩንታል ወይንም ከ45 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጀው የሲሚንቶ አቅርቦት የሚከናወነው በህዋሃቱ የመሶቦ ሲሚንቶ እንደሆነ ሪፖርተር ራሱ ሳይቀር ዘግቧል (The Reporter – English Edition, Saturday, 14 May 2011)። መሶቦ ብቻውን ለምን የግድቡ አቅራቢ ሆነ ብሎ መጠየቅ አዋቂነት እንጂ ዘረኝነት አይደለም። በተመሳሳይ መልኩ የኤሌክትሮሜካኒካል ስራው እና የግንባታውን ግማሽ ወጭ የሚሸፍነው ስራ ደግሞ የሚሰራው በህዋሃቱ የመከላከያ እና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ነው። ሌሎች የግል ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ሳይደረግ የትግራዮች የግል ንብረት የሆነው የመከላከያ እና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ብቻ ለምን ተመረጠ ብሎ መጠየቅ ጠባብነት ሳይሆን ምክንያታዊነት ነው። ስለዚህ አንድ የአማራ ተወላጅ 1 ብር በለገሰ ቁጥር 1 የህዋሃት ኩባንያን እያደለበ እንደሆነ ሊገነዘብ ይገባል። በዚያውም ህዋሃት የሚባል ገዳይ ቡድንን በኢኮኖሚ እያፈረጠመ የአምባገነንነት ህይወቱን በማራዘም የመከራ ቀንበርን ማርዘም እንደሆነ መረዳት ያሻል።

በረጅሙ ስናየው ደግሞ የአባይ ግድብ ማለት የታላቁ የትግራይ ሪፓብሊክ ማስተር ፕላን እቅድ አንዱ አካል ነው። በፕላኑ መሰረት ቤንሻንጉል ክልል ወደ ትግራይ ክልል ይጠቃለል እና አባይም የትግራይ የመብራት ማእከል ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው። ይህ ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን እነ መለስ ገና በ1968 ለትግል ወደ ደደቢት ሲገቡ ጀምረው ያቀዱት እና አሁን ያሉት ግልገሎቻቸው በሰፊው እየሄዱበት ያለ የረጅም ጊዜ እቅድ ነው። በየመማሪያ መጽሃፍቶች የሚንሸራሸረውን ካርታ ልብ ብሎ መመልከት ብልህነት ነው። ትግራዮች እንደሆኑ ስልጣናቸውን እንደሚያጡ ካሰቡ መገንጠል እንጂ ትእቢታቸውን አስተንፍሰው ከሌላው ህዝብ ጋር በእኩልነት መኖር እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ አሳይተዋል። እናም ይህንን ሁሉ ጉድ ስናይ ወያኔ በቅርብ ጊዜአት እስካልተወገደ ድረስ አማራ ከአጭርም ይሁን ከረጅም እቅድ አኳያ ከአባይ ግድብ የመጠቀመው ነገር ላም አለኝ በሰማይ አይነት ነው!

*ማሳሰቢያ
ይህ ጽሁፍ የተጻፈው ጨለምተኛ የሆነ እይታን ለማስተላለፍ ሳይሆን አባይን እና ፖለቲካን አታገናኙብን ለምትሉ የዋህ አማራዎች ነው። አንድን ነገር ስናይ በጥንቃቄ እና መረጃ ላይ ተመስርኩዘን መሆን እንዳለበትም ለማሳሰብ ጭምር ነው። ግድቡ እንዲሰራ የምንፈልገውን ያክል ወያኔን ማስወገድም ቅድሚያ ማግኘት ያለበት ተግባር መሆኑን መረዳት ያሻል። ያለበለዚያ ገንዘባችንንም ነጻነታችንንም አስረክብን የዜሮ ድምር ውጤቶች እንሆናለን!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s