ከ500 ኩንታል በላይ የአልሚ ምግብ በስልጤ ወረዳ ኃላፊዎች ተመዘበረ

save

በአየር ጸባይ ለውጥ የተነሳ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ዝናብ ያላገኘችው ኢትዮጵያ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ በመማጸን ላይ ትገኛለች፡፡ድርቁ በአገሪቱ ርሃብ በመፍጠሩም እንስሳት ሞተዋል፣ወላጆች ለልጆቻቸው የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ለልመና ተዳርገዋል በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎችም በርሃብ ምክንያት እስከወዲያኛው ያሸለቡ ህጻናትና አጥቢ እናቶች ስለመኖራቸው እየተነገረ ነው፡፡

እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ከሆነም ከ450.000 የሚልቁ ህጻናት ወተትና ምግብ ማግኘት ባለመቻላቸው የሰውነት ክብደታቸውና ምግብ የመመገብ አቅማቸው በመዳከሙ አልሚ ምግቦችን ማግኘት ወደሚችሉባቸውና የባለሞያዎች ክትትል ወደሚገኝባቸው ቦታዎች መወሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ነገር በኢትዮጵያ የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እጅግ በጣም ውስን በመሆናቸው ህጻናቶቹን በሙሉ ወዳሉት በጣት ወደሚቆጠሩ ጣብያዎቹ ማስገባት አልተቻለም፡፡

ይህ ችግር በከፍተኛ ደረጃ ከሚታይባቸው ክልሎች አንዱ በሆነው በስልጤ ዞን የአልሚ ምግብና የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ከ26.000 የሚበልጡ አጥቢ እናቶችና ህጻናት ይገኛሉ፡፡በእርዳታ ከተገኘ የአልሚ ምግብ ውስጥም በስልጤ ለሚገኙ ህጻናትና እናቶች እንዲከፋፈል በአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ አማካኝነት ለየቀበሌዎቹ አልሚ ምግቦቹ በኩንታል እየተቆጠሩ ተከፋፍለዋል፡፡

የአልሚ ምግቦቹን የተቀበሉት የወረዳው ቀበሌዎች ኃላፊዎች ከነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር 500 ኩንታል አልሚ ምግብ ለተጎጂዎቹ ከመድረሱ በፊት አየር በአየር ማሸጋገራቸውንና የምግቡን ሽያጭ መከፋፈላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡በዚሁ ሰበብ ቅሬታ የቀረበለት የዞኑ የአደጋ መከላከል ቢሮ አንድ የወረዳውን ኃላፊ ሲያሳስር አንደኛው ከአካባቢው መሰወሩ ታውቋል፡፡

የተፈጠረውን መጥፎ አጋጣሚ በመጠቀም በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ሹማምንት ለተጎጂዎች እንዲያከፋፍሉ የሚሰጣቸውን የእርዳታ እህል ፣ወተትና የምግብ ዘይት በመቸብቸብ ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ በ1977ቱ ድርቅ ለተጎጂዎች የተላከን የእርዳታ ምግብ በመሸጥ የጦር መሳሪያ መግዛቱን የሚያስታውሱ ሰዎች አሁን የእርዳታ እህል በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው አዋሉ የሚባሉ ኃላፊዎችን በመያዝ የመቅጣት ሞራሉን ስለማግኘቱ ይጠይቃሉ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s