የትግራይ “ልማታዊ” የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና የወልቃይት ጠገዴ ህዝብን የማጥፋት ጥማታቸው!

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር  ኢትዮጵያ

ይህን ፅሑፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ አሳዛኝና አጸያፊ ድርጊት በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ መሀል ሲፈጸም በማየቴ ነው። በወያኔና ማስተዋል በተሳናቸው የትግራይ ደጋፊዎቹ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዘሩን የማጥፋት ውሳኔዎቻቸውና ዘመቻቸው ስላዘንኩና ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ ጭምርም ነው። በእርግጥ በዚህ የአማራ ህዝብ ላይ ከ1972 አ/ም ጀምሮ በተለይ ደግሞ ከ1983 አ/ም ጀምሮ ማንም ኢትዮጵያዊ ወገኑ እንዳይሰማ በማድረግ ሰፊ የሆነና የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውንና በዚህ የእግዚአብሔር ህዝብ ያልፈጸሙት የግፍ አይነት እንደሌለ በቅርቡ በተለያዩ ፀሓፍትና ሚዲያዎች እየተረጋገጠ ያለ ሀቅ ነው።

ወያኔና የትግራይ ሰዎች በ25 አመታት ውስጥ ሙሉ ገድለውት፣ አስረውት፣ አሰድደውት፣ ደብደበውት፣ ንብረቱን አጉዘውበት፣ ሴት ልጆቹ ደፍረውበት፣ መሬቱን ቀምተውት እንዲሁም ልዩ ልዩ አይነት ስቃይ ፈጽመውበት ደሙን ጠጥተውና አፍሰው የማይረኩበት እንዲያውም የበለጠ የሚጠሙበትና የሚሰክሩበት የኢትዮጵያ ህዝብ ማን ነው ቢባል መልሱ በእርግጠኝነት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ነው። የሰው ልጆች ሊያምኑት ቀርቶ ሊያስቡት ከሚችሉት በላይ እጅግ እጅግ በጣም የከፉ የተባሉ ዘግናኝ ግፎችና በደል የደረሰበት ህዝብ ነው። እንዲህ ስል ታድያ በሌላው የኢትዮጵያ ወገኖቼ ላይ በየቦታው የደረሰው ስቃይና ግፍ እረስቼእንዳልሆነ ታሳቢ መሆን አለበት።

ከአንድ አመት ከ6 ወራት በላይ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ኮሚቴ አቋቁሞ በግድ የተነጠኩትን የአማራ ማንነቴ ይከበርልኝ ብሎ ለትግራይ ክልል ከዛም ለፌደረሽን ምክር ቤት የአማራ ማንነት ጥያቄ ለማቅረብ ችሏል። አሁን ግን በጣም ያሳዘነኝ ጉዳይ በቅርቡ ይሔን ተከትሎ የትግራይ መንግስት ጥያቄውን ለማዳፈን ጥያቄውን በአስተዳደራዊ በደል ስም በማድበስበስ ህዝቡ በወከለው ኮሚቴ የተለያዩ የሽብር ስሞችን በመለጠፍ ከወከላቸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ በሕጋዊ ኮሚቴ አባላቶቹና መላው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ አፈና፣አዛውንትን በአስተዳደርና ባልታወቁ ታርጋ በሌላቸው መኪኖችም ጭምር ገጭቶ በመግደል፣በጣት በሚቆጠሩ ተወላጅ ካድሬዎች ስም የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ‘ትግሬ ነን’ ብሎ በሚዲያ በማስነገርና ልዩ ቀረጻ በማዘጋጀት ባለው ሚዲያን የመቆጣጠር የበላይነት የተሳሳት የውሸት መረጃ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለትግራይ ህዝብ አዘጋጅቶ ማስተላለፍ፣ እስር፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ ስደት፣ ማሸማቀቅ፣ የንብረት መወረስና ልዩ ልዩ መካራዎችን  የሚያደርስ ሴራዊ ፕሮግራም ነድፎ ህጋዊ ጥያቄው አቅጣጫው እንዲቀይር ይህ ቀረሽ የማይባል ከባድ ጫና ሲያደርስ ቆይቷል።

ይሔን ሲያደርግ የትግራይ ልዩ ኅይል፣ የትግራይ ሚሊሺያ፣ የትግራይ አጋዚ ጦር፣ የሱዳን ደህንነቶች፣ የትግራይ የድሮ ታጋዮች፣ አዲስና ነባር የመከላከያ ስልጡን ሰራዊትና ጀሌዎችን እየተጠቀመ ነው። ተያዥ ማስረጃ ከመስጠት አንጻር ከትግራይ ባዶ እጃቸውን ጥብቆ ለብሰው በህዝቡ ውስጥ ‘ልዋጭ! ቆራሊዮ!’ እያሉ እየቃተቱ ሲዞሩ የነበሩት በወልቃይት ጠገዴ በዳንሻ ከተማ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን እየተደፋላቸው  በወራት ውስጥ ሊታመን የማይችል ሀብት አካብተው ህዝቡን እያስጨረሱ ያሉት ከጀሌዎቹ ሲቪል ደህንነቶች ዉስጥ ለምሳሌ ንጉሰ ገብረሂወት  የተባለ በአሁኑ ስአት ባለወርቅ ቤት የሽሬ ተወላጅ፣ ከንጉስ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሚሰራው ሃዱሽ ትካቦ የተባለ በአሁኑ ስአት ባለቡቲክ፣ የማነ አበራ፣ተድላ ካሳሁን፣ተክላይ ሃበሽና ገብረእግዚአብሔር ነጋሽ በጥቂቱ ለምሳሌ ያህል የሚጠቀሱ ናቸው።

እስካሁኗ ስአት ሃይ ባይ በሌለው ወንበዴ የክልሉ ፈርዖን እየተጨፈጨፉ ባሉበት ሁኔታና በየደረጃው የሚገጥማቸውን መጉላላቱንም ተቋቁመው ህገ-መንግስቱን ባከበረ መልኩ በጣም በከፍተኛ ትዕግስት ጥያቄያቸውን ህጋዊ ሆነው እያቀረቡ የወያኔን ውስብስብ የውንጀላ ሴራዎችን በመበጣጠስ ለሚታገሉና ለሚያታግሉ በመጀመሪያ በፈተና አጽንቶ በሞት ባህር ለሚያሻግር ለልዑል እግዚአብሔር በመቀጠል ደግሞ ለጠንካራው ኮሚቴና ለጀግናውና ትዕግስተኛው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከፍ ያለውን ምስጋና እንዳደርስ ይፈቀድልኝ።

ይሔን ካልኩኝ ብሗላ ወደ ዛሬው የፅሑፌ ትኩረት ልመልሳችሁ ወደድሁ። የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ አንድ የትግራይ የፖሊቲካ ሰው ነኝ ያሉ በስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ “90 በመቶው የትግራይ ህዝብ ‘ከወያኔ ውጭ መኖር አንችልም!’ ብሎ ያምናል፤ ታድያ ለምን በትግራይ ህዝብ ላይ የመልካም አስተዳደር ክፍተት እንዲኖር እናደርጋለን?” ብለው ነበር። እኛ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብም ወያኔ የትግራይን ህዝብ ልቦና በምን መንገድና አካሄድ እንደሰለበው የምናውቀው ነገር ባይኖርም እንኳ የምናውቀው እውነት ግን የትግራይ ህዝብ ‘ካለ ወያኔ መኖር አንችልም’ ብለው እንደሚያምኑ ነው።

በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ መሃል በሰፋሪነትም በወራሪነትም ብቻ በተለያየ መንገድ መጥተው የሚኖሩት ጥጋበኛና ተስፋፊ ‘የትግራይ ሰዎች’ ግን “ወያኔ ምርኩዛችን ነው፤ ወያኔ ክብርና ኩራታችን ነው፣ ወያኔ ኑሯችን ነው፣ ወያኔ ዋስትናችን ነው” ሲሉን ነው የኖርነው እየኖርንም ያለነው። እኛ የወልቃይት ጠገዴ አማሮች በዚህ አቋማቸው ምንም አይነት ችግር የለብንም የፈለጉትን የፖሊቲካ ፓርቲ መደገፍና የፈለጉትን ሓሳብ ማራመድ ይችላሉ። ነገር ግን እነርሱ ይህን ሲያደርጉ እኛን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ እየገደሉንና የወግኖቻችን ሬሳ እንኳን በወግ በስርአቱ እንድንቀብር እየፈቀዱልን አይደለም። በቃ የኛን ዘር በተለያየ መልኩ እያጸዱ ሃብት ንብረታችንን እየወረሱ መኖር መውደዳቸውን ነው የማንቀበለው!!! የተለያየ አይነት ግፍና መከራ የደረሰብንም አሁንም እየደረሰብን ያለውም በእነዚህና በአስተዳደሩ ነው።

አሁን አሁን ደግሞ ጥቃቱ እየደረሰብን ያለው ከማንጠብቀውና ካላሰብነው አቅጣጫ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመሸጉ ከ‘ልማታዊ የትግራይ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች’ በኩል ነው። ወያኔ የትግራይ የቤተ- ክህነት ሰዎችን ሳይቀር ልቦናቸውን አጥተው ድንዙዛን ካድሬዎች ማድረግ የቻለ የሴጣን ድርጅት ነው። የተለያዩ አይነት ሆድ-አደር ካድሬዎች በቅድስት ቤተ-ክርስቲያኒቱ ሰርጎና አሰርጎ በማስገባት ተደማጭነት ያላቸውን የተለያዩ ብዙሓን ግእዝ ቀመስ  ምድራዊውን ውዳቂ ወያኔን የሚባርኩና የሚቀድሱ የእግዚአብሔርን ቤት ግን የሚያረክሱ ‘ልማታዊ የትግራይ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች’ ማፍራቱ በእኛ በወልቃይት ጠገዴ በሚገኙ አቢያተ-ክርስቲያኖቻችን የሚታይ እሙን እውነታ ነው። ሲከፋን ሄደን አምላካችንን አመስግነን እንዳንጸናና እንኳን በዚያ መሃል የሴጣንን ስራ የሚሰሩ ሴጣንን የሚባርኩ ሴጣናውያን ልማታዊ አገልጋዮቹ ህሊናችንን ለማቆሸሽ የሚሞክሩና ህልውናችንን በእጅጉ የሚፈታተኑ ዘረኛ፣ ግዜያዊ ምድራዊውን ፍርፋሪ የሚቃርሙ፣ የተለያየ አስተዳደራዊ ችግር የሚፈጥሩና ጥጋበኛ ፈሪሳውያንና ጸሓፍት አስቀመጦልናል።

በእርግጥ እንኳን በዚህ ግዜ ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን አገልግሎት ጥለው የእግዚአብሔርን ኅይል በመናቅ በራሳቸው የኅይል ትምክህት ድል ለማድረግ ክህነታቸውን አፍርሰው ደርግን ለመውጋት በደርግ ዘመን ጠብመንጃ አንስተው ታጋይ የሆኑ መአት ቀሳውስትና ዲያቆናት እንዳሉ ይታወቃል። ነገ ጥሏቸው ለሚያልፍ ወያኔ በአመጻ እዚህ አድርሰውታል፤ እንግዲህ እግዚአብሔር ደግሞ በአመጻቸው ምክንያት  በነዚህ ‘የጥፋት ልማታዊ ሰዎች’  ላይ ምን ሊፈርድላቸው እንዳሰበ እርሱ ብቻውን ያውቃል። እኛ ግን በፈጠሩብን መከራ ውስጥ ሆነንም ስለነርሱ ያለ እረፍት እየጸለይን ነው። ባልፉት 25 አምታት ወያኔ የትግራይን ህዝብ አይምሮ እራሱና አማካሪው ሴጣን ብቻ የሚያውቁት ‘አጃክስና ኦሞ’ ተጠቅሞ የትግራይን ህዝብ ልብና አይምሮ እንዲህ በቀላሉ ሙልጭ አድርጎ አጥቦ የራሱን የጥፋት ዕቅድ መጫን የሚቻልበት የእባብነትም የእርግብነትም ባህሪይ ያለው መራዥ አሳ ማይህበረሰብ መፍጠር ችሏል።

እንግዲህ ከላይ በድፍረት እንዲህ እንድል ያስገደዱኝ እማኝና ግልጽ ማስረጃዎችን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ። የመጀመሪያው ማስረጃ ከወያኔ እጅ አፈትልኮ በወጣው “ህወሓት በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ ያቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ” በሚል ርዕስ በወልቃይት ጠገዴ ውስጥ በሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናትና በህዝበ-ክርስቲያኑ ላይ በስውር በውስጣዊ አሰራር በትግራይ የሐይማኖት አባቶች ሊተገበሩ የሚገባቸው ግዴታዎች ተብለው ከተቀመጡት መርሃ-ግብሮች መካከል ሲያስቀምጥ “በአካባቢው (በወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ማለቱ ነው) አብዛኛው የኦርቶዶክስ ሐይማኖት እምነት ተከታይና የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆኑ በአብያተ-ክርስቲያናት ላይ የሚደረጉት ስብከቶችና አገልግሎቶች ከአማርኛ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲሆኑ በማድረግ በትግርኛ እንዲገለገሉ ማድረግ። በአከባቢው ወደሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት የሚመደቡ ገበዝ፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ከአካባቢ ሰዎች እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ አገልጋዮች ከሁሉም የደጋው የትግራይ አካበቢ  የሚመደቡበት ሁኔታ በማመቻቸት የመስበኪያ ቋንቋ ትግርኛ እንዲቆጣጠረው ማድረግ። ይህም ማለት ያ አሁን ያለው የአካባቢው የአብያተ-ክርስቲያናት አገልግሎት የአማርኛ ቋንቋ የበላይነት የሚያራምዱ የጎንደሬዎችና የጎጃሞች ቋንቋ ለትግርኛ  ቋንቋ የሚቆጣጠረው ስለሆነ ነው” የሚል ይገኝበታል” (ምንጭ፦ http://welkait.com/?p=4463) በማለት ነበር።

ሁለተኛው ማስረጃ ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አይደለም ሰላማዊ ሰልፍ የአማራ ማንነቱን ስለ ጠየቀ ብቻ ከላይ በትንሹ የጠቀስኩትን ግፍና የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስበት በአንጻሩ ደግሞ በወልቃይት ጠገዴ የሚገኙ ሰፋሪዎችን ጨምሮ ከትግራይ በመቶዎች በሚቆጠሩ መኪኖች እየተጫኑ በተለያዩ የሙዚቃ ባንዶች ታጅበው በህዝቡ መሀል ብጥብጣዊና አሽማቃቂ የዛቻና ስድብ ጦርነታዊ ስልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። በእርግጥ እነርሱን ማንም ‘እናንተ ትግሬ አይደላችሁም አማራ ናችሁ’ ያላቸው አካል የለም። የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ተወላጅ መስለው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደናግሩ ይልቁንስ እውነትነት የሌላቸው አሳሳች እባቦች ናቸው እንጂ። ድርጊታቸው ሁሉ ህሊና ቢስና መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የአለም ህዝብ የሚያወግዘው ነው። የግፋቸው ብዛት ከንቱነታቸውን ሲገልጡት ደግሞ ሰልፋቸውን ተቀላቅለን እራሳችንን እንድናወግዝና እንድናጠፋ ካልሆነ ግን ‘ለሞት እንደሚነዱን’ ሲነግሩንም ለሞት መነዳቱን መርጠን “ሰልፉን አንቀላቀልም” ብለናቸዋል፤ ‘ትግሬ ነን’ ሲሉን “እውነት ነው ትክክል ብላችሗል እናንተማ ትግሬ ናችሁ፤እኛ ግን አማሮች ነን” ብለናቸዋል።

በዚህ መሀል ግን በጣም ያስገረመንና ያሳዘነን ነገር አሁንም ልማታዊ የሆኑትን ወያኔ ‘የቤተ-ክስርቲያን አገልጋዮች’ ጉዳይ ነው። በሁመራ፣ ዳንሻ፣ ማይካድራና አዲ-ረመጥ እሊህ ልማታዊ ‘የትግራይ የቤተ- ክስርቲያን አገልጋዮች’ ያን ጦርነታዊ ሰልፋቸውን ልብሰ-ተክህኖ ለብሰው፣ ታቦት ተሸክመው፣  የመለስን ፎቶ ይዘውበተለያዩ መፎክሮችና ባንድ ታጅበው በማይክሮፎን ውግዘታቸውን መለስ አልሞተም የመልስ ራእይ እውን ሆኖ ይኖራል፤ የወያኔ ጠላት ሴጣን ብቻ ነው፤ጠላትን የምናጠፋ ብዙ ሚሊዮን መለሶች አለን ፤  እናንተ ታውቁናላችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ! ትግሬነትን ካልፈለጋችሁ ከዛሬ ጀምሮ አገራችን ትግራይን ለቃችሁ ውጡ፤ ለሴጣን አንበረከክም” እያሉ ሲያሰሙ ለእኛ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ ተአምር ነው የሆነብን። በነገራችን ላይ የኢህዴግ ኮሙኒኬሽን ሚኒስተር አቶ ጌታቸው ረዳ ለኦሮሞ ህዝብ “የተለቀቁ ጋኔሎች” ማለታቸውን ነው ትዝ ያለኝ። ሲጀመር የሚመሩትን ህዝብ ሴጣን ጋኔል እያሉ መምራት እንደማይቻልና ወያኔ የፈለገውን ነገር ቢያደርግም ምስጥ እንደበላው እንጨት በስብሶ መውደቁን የሚያስረዳ ለኢትዮጵያ ህዝብ የምስራችን የሚነግር ሁኔታ ነው።

ህሊናዬም በመቀጠል ወደ ሁላችንም የምናውቀውው የጣልያን ፋሽስት ኢትዮጵያን የመውረሩ ታሪክ ወሰደኝ። የሮማ ካቶሊክ ቤት ክርስቲያን ፋሽስት ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን እንዲያጠፋ ሰራዊቱንና መሳሪያውን ባርካ ቀድሳ በመላክ በአዲስ አበባ በአንድ ቀን ከ30,000 በላይ ህዝብ ማለቁ ትዝ አለኝ። ለዚህ ድርጊቷ የሮማ ካቶሊካዊት ቤት ክርስቲያን እስካሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ አለመጠየቋ አጠያያቂ በሆነበት ግዜ ከዚሁ ትውሳታዬ ጋር ተገጣጥሞ በትውስታዬ ላይ ክው ብዬ እንዳዝን ያደረገኝ ነገር ደግሞ “ልማታዊው ፋሽስት ፓትሪያርኩ አባታችንiii” አባ ማቲያስ ለሮማ ፖፑ ‘የድሮ ፍቅራችንን እንመልሰዋለንi’ ማለታቸውን ቅድስና በራቀው በመለሳዊ መፎክራቸው መናገራቸውን ሳስብ ነበር። ‘የድሮ ቅሬታችንን በይቅርታ እናስተካክለዋለን!”’ ሊሉ አስበው ይሆን ብዬ ማሰብ ልጅምር ስል ግን ራሴን ማሞኘቴን ቁልጭ ብሎ ታየኝ!!! በፍጹም እሊህ ‘ልማታዊ አባት’ ሆን ብለው ያሉት ‘ፍቅርiii’ ያሉት ነገር ነው እንጂ። በዛ ላይ ይህ ሁሉ የሚሆነው ከሲኖዶስ ፈቃድና ይሁንታ  ውጭ ተጋብዘው እዛው ጣሊያን ውስጥ የፍቅሩን አጀንዳ በማጠናከር ጉዳይ ባካልም በሀሳብም እንደተጠመዱም ታሰበኝ። በዚያ ላይ የጣሊያኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ወያኔን የመጎብኘት ጉዳይም ውር አለብኝ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አስገደ ገስላሴ የተባሉ የአረና ፓርቲ አመራር “ጣሊያን ጉድ ሰራችን” በማለት ዛሬ መጋቢት 27 በፌስቡክ ገጻቸው ላይ “የጣልያን የተቀበሩ የድሮ ንብረቶች ፍለጋ በትግራይ ተራሮች ቁፋሮ እንዲካሔድ ትዕዛዝ ተላልፏል” ካሉ ብሗላ “ይህም  በቁፋሮ  ከሚገነው ንብረት 60 በመቶው ለቆፋሪው  ሲሆን 40 በመቶው ደግሞ መንግስት እንደሚወስድ” በመተንተን “አሳፋሪ ድርጊት ነው” በማለት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸውን አነበብኩ። ይህ ሁሉ መገጣጠም ብቻ ነው ትላላችሁ ወገኖቼ።  ኅሳባቸው የሚደገፍ ቢሆንም ካሁኑ ጽሑፌ በተያያዘ መልኩ በየድረገጹ ከሚጽፉት ጽሑፍ በመነሳት እሊህ ግለሰብ ስልጣን ቢይዙ ግን ሌላኛው የወያኔ ክንፍ መሆናቸውንና በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከወያኔ በላይ ግፍ ሊፈጽሙ ያቀዱ ‘ዲክታተር’ መሆናቸውን አስቤ የኣዞ እንባቸውን ኣይቼ ታዘቤያቸውዋለሁ።

እናማ ወደ የወልቃይት ጠገዴ ጉዳዩ ስመልሳችሁ  ተአምርነቱ ምኑ ላይ ነው ቢሉ አንደኛ የቤተ-ክርስቲያን አባቶች “አስታርቁ፤ በእግዚአሔር ፊት የተወደደችውን መልካም የሆነችውን እውነትን አድርጉ፤ ሰላምን ስበኩ፤ በጎችን ጠብቁ” ተባሉ እንጂ ‘ጥልንና ጦርነትን ስበኩ፤ በጎችን በትኑ” አልተባሉምና። እኛ ግን እሊህ ‘የትግራይ ኣዛውንትና የቤተ-ክርስቲያን ልማታዊ ኣገልጋዮችiii’ የጌታችንና የመድሐኒታችን ትምህርት በተቃርኖው ሲተገብሩ ነው ያስተዋልነው። እሊህ ልማታዊ አገልጋዮች ማስተዋል የተሳናቸው ልባቸው ከንቱ ነገርን የተሞላ የሴጣን ደንገጡርነታቸውን ነው ያስመሰከሩት። እና እነዚህ “ልማታዊ የትግራይ ቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮችም” የጌታቸን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋና ደም በፈተተ እጃቸው እራሳቸውን አርክሰው ለክፉው ስራቸው ፅዋ መሙላት ድምዳሜ ይሆናቸው ግድ ሆኖ ካቶሊካዊት የሮም ቤት ክርስትያን ለሞሶሎኑ የሰጠችውን አይነት እርኩስ ቡራኬ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ  ይጠፋ ዘንድ  ለወያኔና ካድሬዎቹ በዚህ መልኩ እርኩስ ቡራኬያቸውን በይፋ ሰጡ።

እዚህ ላይ ወያኔ ለሐይማኖት አባቶችን የሚያማክሩ እንደ የድሮ የትግርኛ ጋዜጠኛ የአሁኑ የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ዘራፊ የማነ ዘመንፈስቅዱስ የመሰሉ አማሳኝ ወያኔዎች ብቻ ሳይሆን የሚመደበው ከአሸባሪ ቃላት በዘለለ ሐይማኖታዊ ቃላት እንዲጠቀሙ ለወያኔ የሚያማክሩ ልማታዊ የሙስሊምም የክርስቲያንም አገልጋዮች መኖራቸውን እነርሱ እንዲህ በድፍረት የህዝባችን ንብረት በሆነው ቴሌቭዥን ነገር ግን የኛ ባልሆኑ ኅሳዊያን ‘ልማታዊ ጋዜጠኞችና ባለስልጣናት’ በኩል አወቅን። “መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ አይገባም፤ ሐይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም” የሚለውን ታላቅ የኢትዮጵያዉያን የህገ- መንግስታችን መርህም በወያኔና ልማታዊ ካህናትና ልማታዊ ሼኮች በይፋ በዚህ መልኩ በወልቃይት ጠገዴ በይፋ ተጣሰ።

ሶስተኛው ማስረጃም በባለፈው ሳምንት በመቀሌ ከተማ ወልቃይትን የተመለከተ በጣም ብዙ ህዝብ የተገኘበት ስብሰባ አድርገው ነበረ። ከወጣት እስከደቂቅ፣ ከሙሁር እስከጨዋው፣ ከተማሪው እስከገበሬው፣ ከነጋዴው እስከወታደሩ፣ ከወያኔ እስከ አረና ያሉ የትግራይ ሰዎች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ በጣም ብዙ አይነት ሚስጥራዊ ምክክር ከተደረገ ብሗላ እሊህ የትግራይ ልማታዊ የቤተ-ክህነት አገልጋይ ነን ባዮች ተነሱና “ወልቃይት ጠገዴ የአማራ የሚሆኑት ትግራይ የወላድ መሃን ስትሆን ብቻ ነው” ብለው ህዝቡን ካስጨበጨቡ ብሗላ “ትግራይ ግን እናንተን የመሰሉ ጀግኖች ይዛ የመለስ ውርሳችንን ለትምክህተኞቹ አሳልፈን ልንሰጥ አንችልም፤ ትግራይ የወላድ መሀን ስላልሆነች በአካባቢው የሚኖሩትን ትግራይ ያልሆኑት መንጥረን አካባቢው የኛ ይሆናል” ብለው ተናገሩ።

ሊሰሩት የሚገባቸው ስንት ክርስቲያናዊ መርሀ-ግብር እያላቸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዘሩን የማጥፋት አዋጅ በማስረገጥ የዘር ማጥፋት ጥማቸውን ቆረጡ። እሊህ ለሆዳቸው ያደሩ ጠፊ ልማታዊ የቤተ ክህነት ይሁዳውያን የመለስን የጥፋት ራእይ መንገድ ጠራጊዎች ስግብግብ አርዮሳውያን  በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ‘በደም ከተማዋ’ በመቀሌ በድጋሚ ሞትን ፈረዱበት።

እንግዲህ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በልማታዊ  የቤተ ክህነት አገልጋዮች የተፈጸመውን ግፍ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል። እዚህ ላይ ለማሳሰብ እምፈልገው ጥብቅ ጉዳይ  ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ‘በልማታዊ አገልጋዮች’ አገዛዝ ስር መውደቋ ከምንም በላይ በጣም ያሳዝናል!!! በእርግጥ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ሰማያዊት እየሩሳሌም የክርስቶስ ሙሽራ ስለሆነች የገሃነም ደጆችም ቢሆኑ እንኳ አይችሏትም፤ ለዘላለም ጸንታም ትኖራለች። እውነታው እንዲያ ሆኖ ሳለ ወያኔና ልማታዊው የትግራይ ቤተ ክህነት አገልጋዮችና ልጆቻቸው ግን በፈቃዳቸው ባመነጩት ፍላጎት ለሴጣን የማገልገልና የመገዛት ፈቃዳቸው ተገልጦ ጥፋታቸው ፍጹም ይሆን ዘንዳ ይህ ድርጊት መፈጸሙ እነሆ ልብ፣ አይንና ጀሮ ላለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያስተውል፣ ያይና ይሰማ ዘንዳ የትንቢት ፍጻሜ የሆነውን ‘የፍቅር መጥፋት’ መገለጫ ድርጊቶች ኢትዮጵያውያን በሆንን በእኛ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በይፋ መተግበሩ ለህዝባችን ተናገርን። ይህ ህዝብ የዋልድባን ገዳም የሚያነግስ ከሙስሊም ወገኖቹ ‘በፍጹም ኢትዮጵያዊ ፍቅር’ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ህዝብ ነው፤ ይህ ሁሉ ግፍ የሚገባው ሆኖ አልነበረም። ሆኖም ግን ይህ ሁሉ በእርሱ ፈቃድ እርሱ ለሚያውቀው ምክንያት ሆኗልና የእርሱ የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙና ፈቃዱ ይሁን ብለን በፍጹም የምስጋና አርምሞ ስሜት በተመስጦ ውስጥ ሆነን በፍጹም በእምነትና ተስፋ እንገኛለን።

ለአስጨናቂዎቻችንና ገዳዮቻችን ፈርዖናውያን ‘ልማታዊና ተስፋፊ የትግራይ ሰዎች’ ሰጥቶ እንደማይተወንና ወደ ወገኖቻችን እንደሚጨምረን በሙሉ ልብ በመተማመን ፈቃዱንና ጥበቡን እንዲሁም አዳኝነቱን፣  ፍቅሩን፣ ድል አድራጊነቱን፣ ሁሉ ቻይነቱን፣ ነጻነት  መስበኩን፣ ጠላት መምታቱንና ዘላለማዊ ቤት ለልጆቹ ማዘጋጀቱን እያሰብንን በመከራና ሞት ሸሎቆ ውስጥ ብንገኝም በእውነት በከፍተኛ የሐሴት ስሜት ውስጥ ሆነን በልበ-ሙሉነት እየኖርን ስለሆነ ቅዱስ ስሙ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማሪያም ጋር ለዘላለሙ ይመስጌን።

ምንም ቢታጠቁም እግዚአብሔር ያመነ ህዝብ ምን ተአምር መስራት እንደሚችል ልበ-ደንዳና አንበጦቹ በደምብ ያውቃሉ፤ እነሆ ከቅዱሱ የእግዚአብሔር ተራራና የዋልድባ ገዳም ታላቅ ድምጽ ተሰምቷል!!! ጥፋት ለጥፋቱ በዚህ ጉዳይ ማን ሙሉ ለሙሉ ጥፋት ሊገጥመው እንደሚችል እነዚህ ሰዎች በግልጽ ያውቃሉ ብለን ግምት እንይዛለን። ሰፊው የኣማራው ህዝብ እንደሆነ እነርሱ ሰላምን ካልወደዱ ባላወቁት መልኩ ከሚያስቡት በላይ በሆነ በከፍተኛ ህቡእ ዝግጅትና ኣደረጃጀት ቆርጦ መነሳቱን እነሆ ከዛሬ ጀምሮ እነርሱም ይዘጋጁ ዘንድ በግልጽ በዚህች ኣንድ ተለላ መስመር ኣቋማችንን በልበሙሉነት ነገርናቸው።

ያለምንም ወንጀል በዱላ፣ ርሃብና ልዩ ልዩ ስቃይ በከፍተኛ ሙቀት በሁመራ ማረሚያ ቤት ታፍነው የሚገኝቱን የወልቃይት ጠገዴ ልጆች በፍጥነት ልቀቋቸው። ስለ ኢትዮጵያ ሲባል በእግዛብሔር ቅዱስ መንፈስ አዛዥነት በትዕግስት እየጠበቅን ነው፤ ለሰላም የምትተጉ ከሆነ ለሁላችን የሚበጀን በጣም አጭር የተባለ ግዜ ብቻ ነው ያለን። ይህን ስናሳውቅ ስለ ቅድስት ሃገሪቱና ህዝቦቿ ህልውና በከፍተኛ ሁኔታ ከማሰብ አንጻር ነው። እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን እንላለን፤ ውሳኔውና ምርጫው በእጃችሁ ነው ያለውና!!!

ምንም እንኳን ኅጢአተኛ ያልሆነ ሰው በሁላችን መሀል ባይገኝም የነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ቤት ወደው በድፍረት በቅዱስ ቤተ-መቅደሱ እየፈጸሙ ያሉትን የጥፋት ርኩሰት ግን ከመጠን በላይ ያለፈ ስለሆነና ስተው የኔን ቢጤ ጨዋውን የትግራይ ህዝብ እያሳቱ ስለሆነ ፈጥነው ንስሃ ይገቡበት ዘንዳና አገሪቱ ወደ እርስ በርስ ጦርነት የሚነዱ እያንዳንዳቸው ‘የኦራል ጎማዎች’ ሆነው እያገለገሉ እንደሆነ ‘የጥፋት መዐት ደዎል’ እያሰሙ ስለሆነ ክፉው ምግባራቸውን በመርመር የእራሳቸውን ሴጣናዊ ክፉው ድርጊታቸው በራሳቸው አውግዘው ለህዝባቸው (ወያኔን ጨምሮ) እንዲመክሩም ‘እራሳቸው ጠፍተው ሌላውን በከፊል እንዳያጠፉ’  ጨው ለራሽ ስትል ጣፍጥ የተባለውን የኣስተዋይ ኣባቶች ምክርን ላስታውሳቸው ወደድኩ። ኢትዮጵያ  በክብርና በሰላም ከነልጆቿ ለዘላለም ትኑር፤ እግዚኣብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፤ኣሜን!!!

ተግታችሁ ጸልዩ፤ ልዑል እግዚአብሔር ታላቅ ስራን ለመስራት ተዘጋጅቷልና!!!

ተጻፈ በወልቃይት ጠገዴ                           

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር  ኢትዮጵያ

መጋቢት 27 /2008 አ/ም

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s