የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጉዞ የሁለት አሃዝ ዕድገት ወይስ ውድቀት: ከዶክተር አለማየሁ ገዳ የተደረገ ውይይት

በዶክተር አለማየሁ ገዳ

በአዲስ አበባና በለንደን ዮኒቨርስቲዎች የሚያስተምሩ ምሁራን በአገር ውስጥ የመንግስት በጀት ቀጥተኛ ሚና ስላላቸው የውጪ አገራት ኢንቨስትመንቶችና በኢትዮጵያ ብድር ዙሪያ ጥናታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ኢትዮጵያዊው የኢኮኖሚ ባለሞያና መምህር ዶክተር አለማየሁ ገዳ ያቀረቡትን ወረቀት ለንባብ አቅርበናል፡፡

alemayehu-geda
ዶክተር አለማየሁ ገዳ

ዶክተር አለማየሁ በእንግሊዝ መንግስት ዲፓርትመንት ኦፍ ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት የተወሰነ ድጋፍ የሚደረግለት አገር በቀል የሲቪክ ማህበር ባዘጋጀው ለህዝብ ክፍት በተደረገ ውይይት ተገኝተው ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከውጪ በሚገኝ ብድር ላይ ክፉኛ በመተማመን ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን ታዋቂው የኢኮኖሚ ባለሞያ ገለጹ፡፡

‹‹ቻይናን እንውሰድ ለመሰረተ ልማቶች የሚውል ከ17 ቢልዮን ዶላር በላይ ለኢትዮጵያ መንግስት አበድራለች፡፡የእኛ አጠቃላይ ኢንቨስትመንት ከአገሪቱ አመታዊ ምርት 40 ከመቶ ሲሆን መጠበቂያ ውስጥ የሚገባው ከ10-20 ከመቶ የሚሆን ነው፡፡

ወደ አገር ውስጥ የምናስገባው 13 ቢልዮን ዶላር ወጪ በማድረግ ቢሆንም ወደ ውጪ ከምንልከው የምናገኘው 3 ቢልዮን ዶላር ነው፡፡ የሚፈጠረውን ግሽበት የሚሞላውም በዚህ ነው፡፡

‹‹እንደ ቻይና ያሉ አገራ የሚሰጡትን ብድር ቢያቆሙ ነገ ምን ይፈጠራል? ለምሳሌ የቻይና መንግስት ነገ ኢትዮ ቴሌ ኮምን ሽጡልኝ ወይም ከአየር መንገዱ የተወሰነ አክሲዮን ስጡኝ አልያም የእኔን አውሮፕላኖች ግዙኝ እምቢ ካላችሁም ብድር መስጠቴን አቆማለሁ ብትለን ምን ልናደርግ ነው ?

በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ አገሪቱ ትወድቃለች፡፡

ወደ አገር ውስጥ ከምናስገባቸው ነገሮች መካከል 77 ከመቶ የሚሆኑት በጣም አስፈላጊያችን የሆኑ ናቸው፡፡የነዳጅ ዘይት ብቻውን 22 ከመቶውን ይወስዳል፡፡ወደ አገር ውስጥ የምናስገባቸውን ነገሮች ለመቀነስ ብንሞክር እንኳን አንችልም፡፡ምክንያቱም አስፈላጊያችን የሆነን ነገር ማስቀረት አንችልም፡፡

ዶክተር አለማየሁ ይህ የማይታሰብ መሆኑን ለማሳየትም ኮሪያዎች ከአመታት በፊት ከአሜሪካ ወደ አገር ውስጥ ያስገቧቸው የነበሩ 75 ከመቶ የሚደርሱ ምርቶችን በአገር ውስጥ በመተካት ከአሜሪካ ጥገኝነት ለመላቀቅ ያደረጉት ጥረት እንደ አገር ትልቅ ዋጋ አስከፍሏቸው ሳይገፉበት መቅረታቸውን አስረድተዋል፡፡

‹‹ኮሪያዊያን ከዚህ ማጥ ሁኔታቸውን በአግባቡ በማጤን ፣በጉዳዩ ዙሪያ ከምሁራኖቻቸው ጋር በመወያየትና የረዥም ጊዜ እቅድ በመንደፍ መውጣት ችለዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስትም ጥራት ባለው ትምህርት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግና የውይይት አቅምን እንዲያሳድግ ዶክተሩ ምክራቸውን አቅርበዋል፡፡

ላለፉት አስርት አመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሁለት አሃዝ ስለማደጉ በባለስልጣናት ይነገር በነበረባቸው ዓመታት ጭምር ገለልተኛ በሆኑ የመስኩ ባለሞያዎች የሚጠቀሰው የእድገት አሃዝ ላይ ስምምነት እንዳልነበራቸው ይታወቃል፡፡

የተወዘፈው ብድር

ዶክተር አለማየሁ በወረቀታቸው ለተለያዮ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ኢትዮጵያ  ከቻይና 17.6 ቢልዮን ዶላር ፣3 ቢልዮን ዶላር ከቱርክ 1ቢልዮን ዶላር ከህንድ መበደሯን ይጠቅሳሉ፡፡

የአለም ባንክ ዳታ እንደሚያሳየው ከሆነም ከ2012-2016 ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ አበዳሪዎች 6 ቢልዮን ዶላር መውሰዷንና ለመጀመሪያ ጊዜም ከዮሮ ቦንድ 1.5 ቢልዮን ዶላር ተቀብላለች፡፡

ኢትዮጵያ ከወሰደቻቸው ብድሮች በተጨማሪ በየዓመቱ በእርዳታ መልክ 3 ቢልዮን ዶላር ታገኛለች፡፡

 

የኢትዮጵያ ወደ ውጪ የምትልከው ምርት ባለፈው ዓመት ካስገኘው 3 ቢልዮን ዶላር በዚህ ዓመት ወደ 2.5 ቢልዮን ዶላር መውረዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ የመንግስታቸውን የስድስት ወራት ሪፖርት ለፓርላማው ባቀረቡበት ወቅት መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡

ላለፉት አምስት አመታት አገሪቱ ከግብር የምትሰበስበው ገቢ 20 ከመቶ እድገት ቢያሳይም ግብሩ ለአገር ውስጥ አመታዊ ምርት የሚያበረክተው አስተዋእጾ 13 ከመቶ ብቻ ነው፡፡ይህ ደግሞ በሰብ ሰሃራን አካባቢ ከሚገኙ አገራት በጣም ዝቅተኛው ነው፡፡

ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ከግብር 6 ቢልዮን ዶላር ሰብስባለች፡፡ከዚህ ውስጥ 25 ሚልዮን የተገኘው ከአየር ባየር ነጋዴዎች ነው፡፡በቅርቡ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን እንዳስታወቀው ከሆነ ግብሩ በአግባቡ መሰብሰብ ቢችል የ3 ቢልዮን ዶላር ብልጫ ማሳየት ይችል ነበር፡፡

እንደ ገቢዎች ባለስልጣን ሪፖርት ከሆነም ካለፈው የበጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ (ከሐምሌ 1 .2006-ሐምሌ 1 .2007 ) መንግስት የተለያዮ ኢንቨስተሮችን ከግብር ነጻ በሆነ መንገድ እቃዎቻቸውን ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገቡ በማድረጉ አገሪቱ መሰብሰብ ይገባት የነበረን 2.4 ቢልዮን ዶላር አጥታለች፡፡

ቻይና ምን ያህል አገዘችን?

ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ባለወፈው ታህሳስ ወር ባወጣው ሪፖርት ከኢትዮጵያ በየአመቱ 2 ቢልዮን ዶላር በህገ ወጥ መንገድ እንደሚወጣ አስታውቋል፡፡

ስራ ፈጠራና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለኢትዮጵያ በጣም መሰረታዊ ነገር ነው፡፡ከአገሪቱ 90 ሚልዮን ህዝብ የሚበዛው ወጣት መሆኑ ይታወቃል የሚሉት ዶክተሩ የስራ አጥ ቁጥር 16 ከመቶ መሆኑንም ያወሳሉ፡፡

ከ2003 -2012 ባሉት ዓመታት 93 የቻይና ካምፓኒዎች 600 ሚልዮን ዶላር በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ 69.000 ሰዎችን በቋሚነትና 79.000 ኢትዮጵያዊያንን በጊዜያዊነት መቅጠራቸውን የሚናገሩት ዶክተር አለማየሁ የቴክኖሎጂ ሽግግሩ የተባለውን ያህል አርኪ አለመሆኑን ይገልጻሉ፡፡

በተመሳሳይ ዓመታት ህንዶች በኢትዮጵያ ለ24.000 ቋሚና ለ26.000 በጊዜያዊነት የስራ ዕድል መፍጠራቸውን የሚናገሩት ዶክተሩ የቱርክ 341 ካምፓኒዎች ለ50.000 ሰዎች እድል መፍጠራቸውን ያስታውሳሉ፡፡

ቻይና በአፍሪካ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ በማፍሰስ ላይ እንደምትገኝ በስፋት መነገሩን በመጠቆም ንግርቱን የሚፈትኑት የኢኮኖሚ ምሁሩ በአህጉሪቱ ቻይና ያላት ድርሻ 4 ከመቶ ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡በ2010 በአጠቃላይ ከተገኘው 554 ቢልዮን ዶላር ውስጥ በአፍሪካ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የምዕራባዊያን ካምፓኒዎች መሆናቸውን የተለያዩ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ይከራከራሉ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ለአገር ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በዚህ አመት የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያስመዘግበው እድገት 7 ከመቶ እንደሚሆን መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ነገር ግን የጠቅላይ ሚንስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት ዶክተር አርከበ ዕቁባይ ለብሉምበርግ በሰጡት አስተያየት የኢኮኖሚ እድገቱ ሁለት ድጂቱን ሳይለቅ 11 በመቶ እንደሚሆን መናገራቸው አግራሞትን ይፈጥራል፡፡

የውጪ ብድር

 

መንግስት አሁን የኢኮኖሚው አቅም እንዳለፉት አመታት ጥሩ ካልሆነለት ከሚፈጠርበት ቀውስ ጋር መላተም ይጠበቅበታል፡፡በዚህም በአገሪቱ እየተከናወኑ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በአገር ውስጥ የፋይናንስ አቅም ወይስ ከውጪ አገራት በተገኘ ብድር የሚከናወኑ መሆናቸውም ይታወቃል፡፡

መንግስት ከአገር ውስጥና ከውጪ ያገኛቸውን ብድሮች አበዳሪዎቹ ብድራችንን ክፈለን ወይ የሚተማመንባቸውን እንደ ቴሌ ኮም፣አየር መንገድ፣ንግድ ባንክ፣ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽንና የመርከብ ድርጅትን አክሲዮን ስጠን ሳይሉት መመለስ ይችላል?

ነገር ግን ትልቁ ጥያቄ ሚልዮኖች ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ በሚፈልጉበትና በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች አለመረጋጋትና ቀውሶች የተፈጠሩበት መንግስት የታመመውን ኢኮኖሚ እንዴት ሊያክመው ይችላል የሚለው ነው፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s