ትግሬና ወያኔ – ፕ/ ር መስፍን ወልደማሪያም

 

Mesfin 9 - satenaw

የምንግባባ ባይመስለኝም የመጨረሻ ሙከራ ላድርግ፤— የተባለው ሁሉ ስለ ወያኔ ከሆነ ምንም ልዩነት የለንም፤ ገዳይ፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ … አንካካድም! ልዩነታችን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው፤ ስለወያኔ የምንናገረው ሁሉ ለትግሬዎች ሁሉ ይሆናል የሚለው የተሳሳተ አሰተያየት ነው፤ እኔ በማእከላዊም ሆነ በቃሊቲ ጎነደሬዎች፣ ጎጃሜዎች፣ ወሎዬዎች፣ አሮሞዎች፣ ወላይታዎች … ከወያኔዎች ጋር ሆነው እስረኞችን ሲያሰቃዩ አይቻለሁ፤ ትግራይም ሄጄ ከሌለው የኢትዮጵያ ክፍል የተዘረፈው ሁሉ እንኳን ለትግራይ ሕዝብና ለወያኔዎች ሁሉ አልተዳረሰም፤ ገና ከጥቂት አልጠግብ ባዮች ወያኔዎች አልወጣም፡፡

በሌላ በኩል ሲታይ ወያኔም የተነሣው ‹‹አማራ›› የሚባል ጭራቅ በዘበዘን፤ ብቻውን እየወፈረ እኛን አከሳን በማለት በ‹‹አማራ››… ላይ ወፍራም ጥላቻውን እያስፋፋ በአፈ-ጮሌዎቹ በመለስ ዜናዊ፣ በረከት ስምዖንና ዓባይ ጸሐይ ስብከት ጀሌዎቹን አሳምኖ ነው፤ ወያኔዎች ገና ሰሜን ሸዋ ሲዘልቁ የሚያዩአቸው ሰዎች፣ የሚያዩአቸው ቤቶች ውሸታሞቹ ጮሌዎች እንደነገሯቸው አለመሆኑን ሲገነዘቡ ጥያቄ ያነሡ እንደነበረ ሰምተናል፤ ዛሬም ሌሎች የመለስ፣ የበረከትና የዓባይ ደቀ መዝሙሮች ኢላማውን ገልብጠው በትገሬዎች ላይ በጅምላ እያነጣጠሩ ነው፤ አንድን ከመቶ፣ ዝርዝርን ከጅምላ፣ ፖሊቲካን ከዘር መለየት የሚችል አእምሮ ሳይኖር ከአለንበት ሁኔታ አንወጣም፤ ብንወጣም ከጣልነው ጋር ለመንከባለል ነው፤ ወያኔ ደርግን ጥሎ አልተነሣም፤ እዚያው ከሬሳ ጋር ሲነከባለል ተዳከመ! የተሻልን እንሁን! ወያኔ ሁሉ ትግሬ ነው፤ ትግሬ ሁሉ ወያኔ አይደለም፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s