” ኢንቨስተር ሞላ ኣስገዶም ” – አምዶም ገብረስላሴ

129

ሞላ ኣስገዶም የዴምህት ሊቀ መንበር ሁኖ ለኣመታት በኣስመራ መቆየቱና በ2007 ዓ/ም መጨረሻ ወር ማለት ጳጉሜ 800 የሚያክሉ ወታደሮች ኣስከትሎ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የሚታወቅ ነው።

ወደ ሃገር ቤት ከገባ በኋላም የህወሓት ደጋፊዎች “ጀግና” ሲሉት ሌሎች ኢትዮጵያውያን ደግሞ “ከሃዲ” የሚል ቅጥያ ሰጥተውት ነበር።

ኣቶ ሞላ ኣስገዶም ኣስመራ ሁኖ ሲያሳመራቸው የነበሩ ታጣቂዎች በሰው ሂወትና በሚልዮን የሚቆጠር ንብረት ኣውድመዋል።

ከዚህ የዘለለም የዓረና_መድረክ ኣባላት የሆኑት እንደ ኣብራሃ ደስታ፣ ኣማረ ተወልደና ኣያሌው በየነ “ከዴምህት ጋር ግንኙነት ነበራቹ” የሚል የፈጠራ ክስ ተመስርቶባቸው እስካሁን በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።

ሞላና ዴምህት በትግራይ ክልል ኑዋሪዎችና ንብረቶቻቸው ላደረሱት ጥፋት ከመጤፍ ሳይቆጠር ቀርቶ ከፍተኛ ሽልማትና እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛል።

” ኢንቨስተር ሞላ ኣስገዶም ” የሚል ቅጥያ ያወጡለት የመቐለ ከተማ ኑዋሪዎች ናቸው።
ለቅጥያው ደግሞ የህወሓት “ልማታዊ መንግስት” የሰጠው ከ350 እስከ 400 ካሬ ሜትር የሚገመት መሬትና ለፎቅ መስርያ የተሰጠው ገንዘብ መነሻ ኣድርገው ነው።

ኣቶ ሞላ የተሰጠው መሬት መቐለ ዓዲ ሓውሲ( ማጂክ ትህርት ቤት ፊት ለፊት የሚገኝ ክፍት ቦታ) በተለምዶ “ሙስና ሰፈር” እየተባለ የሚታወቅ ኣከባቢ ነው።
ሙስና ሰፈር የሚል የህዝብ መጠርያ እንዲያገኝ ያስቻለው ኣብዛኞቹ የሰፈሩ ቤቶች ምንጩ ግልፅ ባልሆነ ሃብት በህወሓት ባለ ስልጣናት የተገነቡ ምርጥ ቤቶች ስለ ሆኑ ነው።

የኣስመራ ናፍቆቱ እንዳይነሳበት ነው መሰል ከ1990 ዓ/ም የኤርትራ ቆንስል ፅህፈት ቤት በመቐለ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ቤት ከሞላ መሬት በ150 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ቦታ ነው።
ኣዎ…! ኣስመራ ስትናፍቀው ወደ ቆንስል ፅህፈት ቤቱ ጎራ ብሎ እንዲወጣለት ይረዳው ይሆናል።

ኢንቨስተር ሞላ ኣስገዶም በህወሓት ከፍተኛ እንክብካቤ እየተደረገለት ያለ ሲሆን በተሰጠው መሬት ፎቅ ሰርቶ ልክ እንደ ኣብዛኞቹ የህወሓት ከፍተኛ ባለ ስልጣናት እያካራየ እንዲኖር ይረዳዋል።

ሞላ ኣስገዶም ከዴህምህት ሊቀ መንበርነትና ኮማንደርነት ወደ “ህወሓት ልማታዊ ኢንቨስተርነት” ተሸጋግረዋል።
ከሞላ ጋር ኣብረው የመጡት የዴምህት ታጋዮች የተለያዩ የድጋፍ ቃል ተገብቶላቸው የነበረ ሲሆን ቃሉ ሊከበር ባለመቻሉ ተመልሰው ኤርትራ የገቡ እንዳሉባቸው እየተወራ ነው።

ስእሎቹ ላይ ክፍት ቦታው የሞላ መሬት፣ ቤቱ የኤርትራ ቆንስላ ፅህፈት ቤት የነበረ ቤት ናቸው።

ህወሓት ኣህያውን ፈርተው ዳውላውን እንደሚባለው የዴምህት ሊቀመንበር የነበረው ሞላ ኣስገዶም እየሸለሙ በሰላማዊ መንገድ ለሚታገሉ የዓረና ኣባላት “ኣሸባሪ” እያሉ ማሰር፣ መግደልና ማንገላታት ትጥቅ ትግል እንደ ማበረታታት ይቆጠራል።

ፍርድ ቤት ነፃናቹ ያላቸው እንደ ኣብራሃ ደስታ የመሰሉ የሰለማዊ ትግል ጀግኖች ከእስር ቤት ልቀቁልን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

 

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s