ግንቦት 20 ለአማራ ምኑ ነዉ?

ብዙ ሰዎች የራሳቸውን ጥቅም አስበልጠዉ የወገኖቻቸውን ስቃይ እንዳልተከናወነ በማሰብ ከእዉነታዉ ይሸሸጋሉ፡፡ለአማራ ሕዝብ ግቦት 20 ሰቆቃው እንጂ ነፃነቱ አይደለም፡፡ከግንቦት 20 በሗላ አማራ
1/ በአርባጉጉ,ደንገጎ,አርሲ,ወለጋ,ጅማ እና ሸዋ ላይ ተገድሏል,ከመሬቱ ተፈናቅሏል,ንብረቱ ተቀምቷል፡፡
2/ በቤንሻንጉል እንደ ሽንኩርት ተከትፏል፡፡በቤንች ጉራፈርዳ የጅምላ መፈናቀል እና ግድያ ሰለባ ሆኗል፡፡
3/ የገዛ መሬቶቹ ወልቃይት ጠገዴ እና ራያ በትግሬ ተወስዶበታል፡፡በግድም የትግሬ ማንነት ተጭኖበታል፡፡
4/ ኦሮሞ በኦነግ እና ትግሬ በሕወሀት በሽግግር መንስቱ ሲወከሉ አማራ ግን በማንም ሳይወከል ቀርቷል በፌደራሊዝሙ ላይ መልካም ፈቃዱ ሳይጠየቅ ቀርቷል፡፡
5/ ቋንቋዉ እንዳይስፋፋ ተደርጎበታል፡፡ዛሬ በየክልሉ(በተለይም በኦሮሚያ) ሕፃናት እንግሊዘኛን ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ሲማሩ አማርኛን ግን ከ5ኛ ክፍል መማር ይጀምራሉ፡፡
6/ የራሱ ተወላጅ ባልሆኑ ሰዎች እንዲመራ ተገዷል፡፡ለአብነትም ታምራት ላይኔ ጉራጌ,አዲሱ ለገሰ ኦሮሞ,ተፈራ ዋልዋ ሲዳማ, በረከት ስምኦን ኤርትራዊ እና ሕላዊ ዮሴፍ ኤርትራዊ፡፡
7/ የዘር ማጥፋት እየተከናወነበት ነዉ፡፡ከ5ሚለዮን በላይ አማራ የት እንደገባ ሳይታወቅ ቁጥሩ ቀንሷል፡፡
8/ በግብርና በመሳሰሉት የመንግስት ጫናዎች ከኢኮኖሚዉ ዉድድር ዉጪ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት በደሎች ሁሉ በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀሙት ከግንቦት 20 በሗላ ነዉ፡፡ብአዴን ግን ይሕንን በደላችንን የምንረሳ መስሎት ይብስ ብሎ የባሕርዳር አየር መንገድን በግንቦት 20 መሰየሙ የሚደንቅ ነዉ፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s