ሸጌ ሮባ ‹‹እባካችሁ እርዱን ፣እኛ ተስፋ ቢስ ሆነናል››

ethiopia

በድርቁ ምክንያት የተከሰተው የምግብ እጦት ችግር ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ እየተባባሰ መምጣቱን የገለጹት የእርዳታ ድርጅቶች የአገሪቱ መንግስት የተለያዩ እቅዶችን በመንደፍ የእርዳታ ለጋሾችን ደጅ ቢያንኳኳም የተገኘው ከሚያስፈልገው አምስት ከመቶ ያህሉን ብቻ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

‹‹በአሁኑ ሰዓት 10 ሚልዩን ሰዎች አፋጣኝ የምግብ እርደታ የሚፈልጉ ቢሆንም በየቀኑ ቁጥሩ በመጨመር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ትክክለኛውን አሃዝ ለማስቀመጥ ያስቸግራል››ብለዋል ድርጅቶቹ፡፡

በድርጅቶቹ ገለጻ መሰረትም በድርቁ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሰዎች ችግሩን ለመቋቋም የተለያዩ አማራጮችን በመከተል ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል ፡፡ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት ማስቀረት፣ዛፎችን በመቁረጥ ማቃጠል ከሰል ለማምረት፣ለእርሻ ያስቀመጧቸውን ቁሳቁሶች መሸጥና አካባቢያቸውን በመልቀቅ የቀን ስራ መስራት ወደሚችሉባቸው ቦታዎች መሰደድ የመሳሰሉትን በማድረግ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

የ30 ዓመቷ ሸጌ ሮባ በግብርና ትተዳደር ነበር፡፡ለቲርፈንድ እንደነገረችውም ‹‹ነገሮች ይለወጣሉ በማለት ተስፋ ስናደርግ ቆይተናል፡፡አሁን የምንበላው የደረቀ ነገር ብቻ ነው፡፡የምንጠጣው ውሃ ጨው ነው፡፡ከነበሩኝ 40 በጎች መካከልም 30ዎቹ በድርቁ ምክንያት ሞተውብኛል››ብላለች፡፡

በህይወት የሚገኙት የቤት እንስሳቶቿ በመኖሪያ ቤቷ ሞትን እንደሚጠባበቁ የምትናገረው ሸጌ ‹‹የምናቀርብላቸው ምንም አይነት ነገር ባለመኖሩ እቤት ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ፡፡እባካችሁ እርዱን፡፡እያደረጋችሁልን ስለሚገኘው ነገር በሙሉ ትልቅ አክብሮት አለን፡፡ከእኛ ጎን መቆማችሁን እንድትቀጥሉበት እንማጸናችኋለን፡፡የነበረንን ተስፋ አጥተናል እስካሁን ድረስም የምግብ እርዳ ማግኘጥ አልቻልንም››ማለቷ ተዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ወጥሮ የያዛት ድርቅ የ1977ቱን አይነት ሰብዓዊ እልቂት ሊፈጥር እንደሚችል የእርዳታ ድርጅቶቹ  ከፍተኛ ስጋት ገብቷቸዋል፡፡በ1977ቱ ድርቅ 400.000 የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው አይዘነጋም፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጀመረው የ90 ቀናት ካምፔይን “Act Now. Protect Tomorrow”የሚል ስያሜ በመስጠት መንግስታትንና አለም አቀፍ ድርጅቶችን የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ እየተማጸነ ይገኛል፡፡

‹‹በፍጥነት ምላሽ መስጠት ካልጀመርን የብዙዎችን ህይወት እናጣለን፡፡ድርቅ በመታቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች በአልሚ ምግብ እጦት፣ትምህርት በማጣትና በደካማ የጤና አገልግሎት ሽፋን የተነሳ አደጋ ውስጥ ናቸው››፡፡ብለዋል ድርጅቶቹ ፡፡

ምንጭ ቲር ፈንድ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s