ካንሰር በኢትዮጵያ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው

cancer

ካንሰር ኢትዮጵያዊያንን በከፍተኛ ደረጃ በማጥቃት ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት የቀድሞው የኢትዮጵያ የጤና ሚንስትር ባልደረባ 70.000 የሚደርሱ አዲስ የካንሰር ተጠቂዎች መገኘታቸውንና በየዓመቱም 44.000 ሰዎች ለሞት እንደሚዳረጉ ይፋ አድርገዋል፡፡

‹‹ካንሰር በኢትዮጵያ በመስፋፋት ላይ የሚገኝ ችግር ነው፡፡በአገሪቱ እየተመዘገበ ለሚገኝ አጠቃላይ የሞት መንስኤም 5.8 በመቶውን ካንሰር ይወስዳል ››ያሉት ካንሰርን ለመከላከል በጤና ሚንስትር ስር ለተቋቋመው ቡድን የቴክኒክ አማካሪው ዶክተር ኩኑዝ አብደላ ናቸው፡፡

ኩኑዝ እንደሚናገሩት ከሆነም ከ75 ዓመት በታች ለአጠቃላይ የጤና እክሎች በህክምና ላይ ከሚገኙት የካንሰር ህሙማን 11.3 ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 9.4 ያህሉ በሞት ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ በአብዛኛው ለካንሰር ከሚጋለጡት የህብረተሰብ ክፍሎች ሴቶች እንደሚበዙ ያወሱት ዶክተር ኩኑዝ ‹‹ከካንሰር ጋር በተያያዘ ለሞት ከሚጋለጡት ውስጥ ሁለት ሶስተኛ ያሉ ሴቶች ናቸው››ብለዋል፡፡

የጡት ካንሰር ኢትዮጵያዊያኑን ሴቶች በብዛት እንደሚያጠቃቸው የገለጹት ዶክተሩ በካንሰር ከተመዘገቡት ህሙማን ውስጥ 30.2 % ያህሉን ይይዛሉ ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

የ39 ዓመቷ ማህሌት ከበደ የጡት ካንሰር እንዳለባት በተነገራት ወቅት መደንገጧን በማስታወስ በሰጠችው አስተያየት ‹‹ሁኔታውን ለመቀበል በጣም ተቸግሬ ነበር፡፡አሁን ማገገም ችያለሁ ነገር ግን ሰዎች ወደሞቴ እየተቃረብኩ እንደሆነ ያምናሉ››ብላለች፡፡

በኢትዮጵያ በ118 ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች የካንሰር የመጀመረያ ደረጃ ህክምና እንደሚሰጥ መረጃዎች ቢጠቁሙም በተከታታይነት በስፔሻላይዝድ ደረጃ ህክምና የሚሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በሚገኘው ጥቁር አምበሳ ሆስፒታል መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ዶክተር ኩኑዝ በ2030 ከካንሰር ጋር በተያያዘ 21 ሚልዩን ሰዎች ህክምና ፍለጋ ወደ ሆስፒታሎች እንደሚመጡ በመግለጽ 13 ሚልዩን ያህሉ በካንሰር ሰበብ ለሞት እንደሚዳረጉ መገመቱን ጠቅሰዋል፡፡

ለካንሰር ህክምና ለመድኃኒትና በየጊዜው ለሚወሰድ መርፌ የሚወጣው ወጪ እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑም ኢትዮጵያዊያኑ ወጪውን መቋቋም ተስኗቸው ለሞት እጅ እንደሚሰጡም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s