ሕወሓት በኦሮሚያ ከ800 በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ * 121 ባለስልጣናት ሊታሰሩ ነው

በመላው የኦሮሚያ ክልል የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ቁጣ ተከትሎ ከሕዝቡ ጎን ወግነዋል አልያም ደግሞ የሕወሓትን እርምጃ ላለማስፈጸም ለግመዋል የተባሉ ከ800 በላይ የኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ ወሰደ:: አብዛኞቹ ባለስልጣናት ከነበሩበት የስልጣን እርከን ወርደው ታች እንዲሰሩ የተፈረደባቸው ሲሆን 121 አመራሮችን ደግሞ ለማሰር መዘጋጀቱን ዛሬ የመንግስት ሚዲያዎች ባሰራጩት መረጃ ላይ ተገልጿል::

በነዚህ “ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ” ለሚፐወዙት ባለስልጣናት የተሰጠው ምክንያት በየመሬትና መሬት ነክ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የመንገድ፣ የውሀ፣ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለግመዋል አልያም ደግሞ አልታዘዝ ብለዋል በሚል ምክንያት ይሁን እንጂ የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ግን ከሕዝቡ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ነው ይላሉ::

የኦሮሚያ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫው 708 ከፍተኛና መካከለኛ ባለስልጣናት ከስልጣናቸው እንዳነሳ እንዲሁም 121 የዞን እና የከተማ የወረዳ ሃላፊዎችን ዝቅ ብለው እንዲሰሩ አድርጓል:: ከ708ቱ ውስጥ ደግሞ 121ዱ በሕግ እንደሚጠየቁ የወጣው መግለጫ ያሳያል::

በኦሮሚያ ጋብ ያለ የሚመስለው ሕዝባዊ ቁጣ አልፎ አልፎ በየከተማው ይታያል:: በዚህ ሳምንት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሎ ነበር:: በተለይም ከትናንት በስቲያ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ አዋሮ ካምፓስ ተማሪዎች ሕዝባዊ ቁጣቸውን በስር ዓቱ ላይ ሲያሰሙ ነበር::

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s