አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቁልቁል መምዘግዘጉን አስታወቀ

star

አለም አቀፉ የሞኒታሪ ፈንድ የአገራትን ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት በማስመለከት ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቁልቁል መምዘግዘጉን አስታውቋል፡፡

ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር በ30 ዓመታት የቅርብ ግዜ ታሪኳ ውስጥ አስተናግዳው የማታውቀውን አይነት ከፍተኛ ድርቅ በማስተናገዷ 100 ሚልዮን ከሚገመተው ህዝቧ አምስት ከመቶ የሚሆነው የምግብ እርዳታ የሚፈልግ ሆኗል ያለው አይ ኤም ኤፍ ለዚህም 1.4 ቢልዮን ዶላር መጠየቁን አስታውሷል፡፡

ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ፈጣን የተባለ የኢኮኖሚ እድገት(10.2%)ማስመዝገቧን የገለጸው ተቋሙ በዚህ ዓመት ኢኮኖሚው ወደ 4.5% ማሽቆልቆሉን በአግራሞት አስፍሯል፡፡የኢኮኖሚው እድገት በአገሪቱ የተፈጠረውን ድርቅ ተከትሎ በዚህ አመት 8.1% እንደሚሆን ተገምቶ ነበር ያለው አይ ኤም ኤፍ በ2017 የኢኮኖሚ እድገቱ 7 ከመቶ ይሆናል ተብሎም ተተንብዮ ነበር ብሏል፡፡

አይ ኤም ኤፍ በሪፖርቱ ከአፍሪካ አገራት መካከል አይቮሪ ኮስት፣ኬንያ፣ሩዋንዳና ሴኔጋል ከ6-7 ከመቶ የኢኮኖሚ እድገት በያዝነውና በቀጣዩ ዓመት እንደሚያስመዘግቡ ትንበያውን አስቀምጦላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከወር በፊት የመንግስታቸውን የስድስት ወራት ሪፖርት ለፓርላማው ባቀረቡበት ወቅት ላለፉት አስርት አመታት እንደ ዶግማ ተይዞ የነበረው የሁለት ዲጂት የኢኮኖሚ እድገት ገለጻ በዚህ አመት እንደማይኖር በማውሳት የኢኮኖሚ እድገቱ በአንድ ዲጂት እንደሚሆን መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

በአንጻሩ የጠቅላይ ሚንስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የኢኮኖሚ እድገቱ ዘንድሮም ሁለት ዲጂት እንደሚያስቆጥር መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ ሜይል ኤንድ ጋርዲያን አፍሪካ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s