የጋምቤላዉ ዘግናኝ ጥቃትና የህወሃት ቸልታ | ከሳዲቅ አህመድ

sadik

ያኔ ወጣቶቹ “ያገር አንበሳ የዉጭ እሬሳ!” በማለት ድምጻቸዉን ሲያሰሙ ዱላና እስር እጣ ፈንታቸዉ ሆኖ ነበር። ለወራት በኦሮሚያ ዉስጥ ንጹሃንን ወገኖቻችንን ሲገድል፣ሲጨፈጭፍ፣ሲያሰቃይና ሲያስር የነበረዉ ጀግና ነኝ ባዩ የህወሃት የአጋዚ ጦር ምነዉ ለጋምቤላ ወገኖቻችን ለመድረስ እጅ ወረደዉ? በዚህ ሒደት ዉስጥ አሸባሪው ህወሃት ለዜጎቹ ደንታ ቢስ መሆንኑንን እንረዳለን። በአንጻሩ አሸባሪው ህወሃት አገርን አተራምሶ ሽብር ከመፍጠር በስተቀር ዜጎችን የመጠበቅ ብቃት የሌልዉ መሆኑን አሳይቷል። አሸባሪዉ ህወሃት የደረሰበትን የፖለቲካ ኪሳራ ለመታደግ ወዲያዉኑ ጋምቤላ ገብቶ “አለሁ አለሁ” ባለ ነበር። ግን እራሱን ከሚገባዉ በላይ እዚህም እዚያም በመወጠሩ ይህንን ማድረግ ተስኖታል። ዜጎችን ከዉጭ አጥቂ መከላከል ባለመቻሉ ስስ ብልቱ ታይቶበታል። ህወሃት ቅልብ ጦሩን ጋምቤላ የሚያሰፍረዉ መሬትን ለመቀራመትና የጋምቤላ ህዝብን ለማሽመድመድ እንጂ የጋምቤላ ህዝብ ሲጠቃ ጥቃቱን ለመመከት አለመሆኑን በሚያሳፍር መልኩ አሳይቷል።ጥያቄዉ በኦሮሚያ የተነሳዉ አይነት ንቅናቄ ዳግም ቢጀመር፣ የሰሜኑ (የጎንደር-የወልቃይት) ንቅናቄ ዳግም ቢጠናከር፣ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ህዝባዊ እምቢተኝነት ቢገነፍል፣ ኮንሶዉ ዳግም እምቢኝ ማለቱ ቢያገረሻ፣አፋሩም ሶማሌውም ቢጨመር ህወሃት ይህንን መቋቋም ይችላልን? አላህ ለተጠቁት የጋምቤላ ወገኖቻችን ይድረስላቸዉ።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s