በስኳር ፕሮጀክት ምክንያት መሬታቸውን የተነጠቁ ወልቃይቴዎች ካሳ አለማግኘታቸውን ገለጹ

መንግስት ለመገንባት እቅድ ከነደፈለት የስኳር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በሺህዎች የሚቆጠሩ የወልቃይት ጸገዴ አካባቢ ነዋሪዎች በካሳ መልክ እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረን ገንዘብ ሳያገኙ አመት መቆጠሩን አስታውቀዋል፡፡

Zarema-Dam-Wolqayit-Sugar-8
በምዕራብ ትግራይ ዞን ከአዲስ አበባ 1.200ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ወልቃይት ወረዳ 2600 አባወራዎች በፕሮጀክቱ ምክንያት የመኖሪያ ቦታቸውን እንዲለቁ ከተደረጉ አመት መሙላቱን በመጠቆም የተገባላቸውን የካሳ ክፍያ ግን ማግኘት ባለመቻላቸው ችግር ውስጥ መዘፈቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ ላይ መንግስት ለስኳር ፕሮጀክቱ እፈልገዋለሁ ያለውን 50.000 ሄክታር መሬት በመውሰድ ቅያሬ ቦታ የሰጣቸው ቢሆንም ገንዘቡን ማግኘት አለመቻላቸው ችግር ጋርጦባቸዋል፡፡የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚጠቁመውም ከሆነ በአካባቢው ይገኙ የነበሩ ሰዎች ቁጥር 140.983 ይደርሳል፡፡

የስኳር ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ችግሮችን በማስተናገድ ላይ ከሚገኙ ሶስት የመንግስት ትልልቅ ፕሮጀክቶች ዋናው መሆኑ ይታወቃል፡፡ከሶስት ዓመታት በፊት በፕሮጀክቱ ምክንያት የወልቃይት ወረዳ ነዋሪዎች ከቦታቸው እንዲነሱ ሲደረጉ በተለይም የጸብሪና ጸሊማ ቀበሌ ነዋሪዎች ወደ ቆራሪት በመወሰዳቸው ከአካባቢው ሰዎች ጋር ደም ያፋሰሰ ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡

መሬታቸው በልማት ስም ተወስዶባቸው ለችግር ከተጋለጡት አባወራዎች አንዱ 3.5 ሄክታር መሬቱ ከተወሰደበት በኋላ የተሰጠው 1.75 ሄክታር መሆኑን ይናገራል፡፡ መንግስት በአንድ ሄክታር 18.000 ብር ለመስጠት ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም አባወራዎቹ እስካሁን ድረስ ቤሳቤስቲን አለማግኘታቸውን በምሬት ይናገራሉ፡፡

በቅያሬ መልክ የተሰጣቸው ቦታ ቢሆንም ለሰው ልጅ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ያልተሟሉበት እንደ ውሃ ፣መብራትና የጤና ኬላዎች የማይገኝበት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ተፈናቃዩቹ ችግራቸውን ለክልሉና ለፌደራል መንግስት ለማስረዳት በማሰብም በመደራጀት ማህበር መስርተው አቤቱታቸውን ለማቅረብ በሞከሩበት ሰዓትም የማህበሩ አመራሮች ወህኒ እንዲወርዱ ተደርገዋል፡፡

ከስድስት ዓመታት በፊት ይፋ የተደረገው የስኳር ፕሮጀክቱ እቅድ በስድስት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ቢነገርም  ለፕሮጀክቱ ይፈለጋል በተባለ ቦታ ላይ የሰፈሩ ሰዎችን ማንቀሳቀስ የተጀመረው ሁለት አመታት ዘግይቶ ነው፡፡በእቅዱ የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑና ግድቡ በሚሰራበት ወቅትም በአፈር ድልደላ ስራዎች እንደሚሰማሩ ተጠቅሶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ይህ አለመደረጉ ታውቋል፡፡

የስኳር ፋብሪካው ግንባታው ሲጠናቀቅ በቀን 24.000ቶን ስኳር ሙሉ ለሙሉ የማምረት አቅሙን መጠቀም ሲጀምርም 484.000 ቶን ስኳርና 41.654 ኪዩቢክ ሜትር ኢታኖል በዓመት ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በአሁኑ ወቅትም የቻይናው ሲኤኤምሲ ካምፓኒ የግንባታውን ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የስኳር ፋብሪካዎችን በሶስት የአገሪቱ ክፍሎች ለመገንባት እቅድ የያዘው መንግስት ከወልቃይት፣ኦሞና ጣና አካባቢዎች 19.000 አባወራዎችን አፈናቅሏል፡፡ከተፈናቃዩቹ ውስጥ ተቀያሪ ቦታ ያገኙት ከግማሽ በታች መሆናቸውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ምንጭ ፎርቹን

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s