የጋምቤላው ዕልቂት| የደቡብ ሱዳን እና የኢትዮጵያ ወታደራዊ አመራሮች መወያየታቸው ተሰማ

 Ethnic Murle gunmen

ከልዑል ዓለሜ

በትናንትናዉ እለት የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮች መወያየታቸው ተሰማ:: ዉይይቱ እጅግ የሱዳናዊያን ብቻ ነበር የሚመስለዉ ያሉት ዉስጥ አዋቂ መረጃችን…. ተቆርቋሪነታቸዉ ለሱዳናዊያን የሙርሲ ብሔር ወንጀለኞች የሆኑ ሁለት ወታደራዊ አመራሮች በተለየ መልኩ በድንበር ማስጠበቁ እና የድንበር ማካለሉ ስራን አስረግጠዉ አስቀምጠዋል::

” እንደዚህ ያሉ የብሔር ግጭቶች በሰሜኑ የሱዳን ድንበርና ኢትዮጵያ መካከልም ይፈጠራል ያሉት የኛዎቹ የመከላከያ ጀኔራል ጉዶች ድንበር እስኪካለል ድረስ የሰሜን ሱዳናና የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አብረዉ በጥምረት እየሰሩ እንደሆነና የደቡብ ሱዳኑም ያንኑ እንዲያደርግ ሐሳብ አቅርበዋል”

የጋምቤላ ወገኖቻችንን ከ10 ቀበሌዎች በላይ ዘልቀዉ በመግባት የገደሉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ወይም ወንጀለኞቹ በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እንዲሁም ታፍነዉ በተወሰዱት 103 ሕጻናት ዙሪያ እና የደቡብ ሱዳኑ መንግስት ካሳ እንዲከፍል በመጠየቅ በኩል ያልተሳተፈዉ የወያኔ መንግስት ነገሩን ሆን ብሎ እንዲፈጸም ያደረገ መሆኑን ከስብሰባዉ መንፈስ ለመረዳት ተችሏል።

በመጀመሪያ ደረጃ ጋንቤላን በፌደራል መንግስት እጠቀልላለዉ ያለዉ ህወሃት የክልሉን መከላከያ ሰራዊት በመበረዝ ከቦርደር ላይ እንዲነሱ በማድረግና በምትካቸዉ ምንም አይነት ሰራዊት ሳያመጣ መሰንበቱ! እንዲሁም በሁለቱ ብሔሮች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት አዲስ እንዳልሆነና በማንኛዉም ወቅት እንዲህ ያለ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል መረጃ እያለዉ ጉዳዩን በቸልተኝነት ያለፈዉ የድንበር ማካለሉን ጉዳይ ከጋምበላ ወደ ጎንደር ለመዉሰድ የታለመ ሳይሆን እንዳልቀረ ተንታኞች እየገለጹ ነዉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሙርሌ ብሔረሰብ ታጣቂ የተባሉት ወታደራዊ አቋም ያላቸዉና ልዩ ስልጠና የወሰዱ የደቡብ ሱዳን ወታደርዊ ዩኒፎርም እንዲሁም አንዳንዶቹ የኢትዮጵያን መከላከያ የደንብ ልብስ የለበሱ ሲሆኑ ግድያዉን ከፈጸሙ በኃላ የኢትዮጵያ መከላከያ ፈጽሞ ያለመኖሩን የተገነዘቡት የጋንቤላ ህዝቦች በመተባበር የሙርሲ ብሔር የተባሉትን ነፍሰ ገዳዮች በማሳደድ የመልሶ ማጥቃት እንደፈጸሙ ምንጫችን አረጋግጠዋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s