ፌደራል ፖሊስ ለሰልፍ የወጡትን ዛሬ ጋምቤላ ላይ በጥይት ቆላ | በጋምቤላ ሁከቱ አይሏል

photo

ጃዊ በሚገኝ የስደተኞች ጣቢያ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ሁለት መሞታቸውን ተከትሎ; ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች 15 ኢትዮጵያውያንን (በአብዛኛው የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑ) በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን ተከትሎ የጋምቤላ ነዋሪ ትናንት ጀምሮት የነበረውን ሰልፍ ዛሬም ቀጥሎበት ውሏል::

ቁጥራቸው ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰልፈኞች በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ; በስደተኞቹ ሴቶች ሳይቀሩ ብልታቸው ውስጥ እንጨት ተሸንቁሮ መገደላቸውን በማውገዝ ላይ በነበሩበት ወቅት የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ደርሶ ሕዝቡን ለማስቆም ጥይት ተኩሷል:: ከጋምቤላ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያመለክተው ፌደራል ፖሊስ ወደ ኢትዮጵያውያኑ ሰልፈኞች ላይ በተኮሰው ጥይት እስካሁን የታወቁ 5 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል:: ከ15 በላይ ወገኖችም መቁሰላቸው ተሰምቷል::

በጋምቤላ በተለይ የኑዌርም ሆነ የአኝዋክ ብሄረሰብ አባላት ያልሆኑትና በተለይም የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች በስደተኞቹ ተመርጠው መገደላቸው ሕዝቡን ከፍተኛ ቁጣ ውስጥ ከመክተቱም በላይ ለ2ኛ ቀን አደባባይ ወጥቶ ውሏል:: ከስፍራው መረጃዎችን እንዳቀበሉን ወገኖች ገለጻ በአሁኑ ወቅት ጋምቤላ በፌደራል ፖሊስ ከመወረሯም በላይ ሰልፈኞቹ አልፈው ወደ ስደተኞች ጣቢያ እንዳይሄዱ መንገዶች መዘጋጋታቸውን ነው:::

በጋምቤላ ያለው ሁከት በቀጠለበት በዚህ ወቅት መንግስት ከአንድ ሳምንት በፊት በሙርሌ ጎሳ አባላት የተወሰዱትን 125 ህጻናት ጉዳይ መረጃ እስካለመስጠት ደርሷል:: የመንግስት ሚዲያዎች ከአንድ ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ታግተው የተወሰዱት ህፃናትና ሴቶች ያሉበትን ቦታ አውቆ ከቧሸዋል የሚል መረጃዎችን ያስተላለፉ ቢሆንም ከዚያ በኋላ መንግስት ያለው ነገር አለመኖሩና ህፃናቱም ታፍነው የተወሰዱበት ቦታ በረሃብና በበሽታ ከመጋለጣቸው አኳያ መንግስት ምን እያደረገ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ነው::

ከጋምቤላ ተጨማሪ መረጃዎች ከደረሱን ዘ-ሐበሻ አሁንም ለአንባቢዎቿ ከማካፈል አትቆጠብም::

This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s