አሜሪካ በነአቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ሥጋቷን ገለፀች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት /ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/

የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ በቀለ ገርባና በሌሎች ላይ የሽብር ፈጠራ ክሥ ለመመሥረት መወሰኑ በጥልቅ እንዳሳሰበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ።

 

የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ በቀለ ገርባና በሌሎች ላይ የሽብር ፈጠራ ክሥ ለመመሥረት መወሰኑ በጥልቅ እንዳሳሰበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ረዳት ሚኒስርና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ ቢሮ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና የመብቶች ተሟጋቾችን ለማሳደድ አድራጎት በፀረ-ሽብር አዋጁ ላይ መንጠላጠሉን እንዲያቆም ጠይቋል።

“ይህ አድራጎት – ይላል ከረዳት ሚኒስትርና ቃል አቀባዩ ኪርቢ ቢሮ የወጣው መግለጫ – የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ዕድገት ከማደናቀፈ ይልቅ የሚያጠናክሩ ነፃ ድምፆችን የሚያፍን አድራጎት ነው። ”

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ዜጎቻቸው ለሚያሰሟቸው አግባብ የሆኑ ቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጡና ኦሮምያ ውስጥ በተፈጠረው ሁኔታ ለአንዳንዱ ሁከት የፀጥታ ኃይሎቹ ተጠያቂ መሆናቸውን እንዲገነዘቡ እንደሚመክሩ ሚስረት ኪርቢ አመልክተዋል።

ይሁን እንጂ መንግሥቱ በዚያ ሁኔታ ውስጥ ተሣትፈዋል ያላቸውን ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን እስከአሁን እንዳሰረ ቢሆንም ለተወሰዱት አግባብነት የጎደላቸው የኃይል እርምጃዎች በተጠያቂነት የተያዘ አንድም የፀጥታ ባለሥልጣን እንደሌለ ኪርቢ ጠቁመዋል።

“እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ደግሞ ለችግሩ ዘላቂ መፍትኄ ለማግኘት የሚያስፈልጉት እምነትና መተማመን እንዳይኖሩ ያደርጋል” ብለዋል ረዳት ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው።

መግለጫው አክሎም የታሠሩት ሰዎች ይደርሱብናል የሚሏቸውን ሥቃይና እንግልቶች የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያጣራና የሕግ አግባብነት ያለውን መብታቸውን እንዲያከብር፤ በታሣሪዎቹ ላይ በማስረጃነት የቀረቡ ጭብጦችን ለሕዝብ በይፋ እንዲያሳውቅ፤ የፖለቲካ ተቃውሞዎችን፤ ለአመፅ ከማነሳሳት ለይቶ እንዲያወጣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እንዲያሳስብ አመልክቷል።

“መንግሥቱ፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ መሣተፍን ጨምሮ የዜጎቹን በሕገ-መንግሥቱ የተቀረፁ መብቶች እንዲያከብር የምናሰማውን ጥሪ በድጋሚ እናረጋግጣለን፤ “መብቶቻቸውን ስለተጠቀሙ የታሠሩትን መንግሥቱ አሁኑኑ እንዲለቅቅ እናሳስባለን” ብሏል የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጫ። መግለጫውን በእንግሊዝኛ ለማምበብ ይህንን ፋይል ይጫኑ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s