የኢራቅ ፓርላማ በተቃዋሚዎች ተወረረ

parlament

 

በሺህዎች የሚቆጠሩ የሻዒት ሙስሊሞች በባግዳድ የሚገኘውን የኢራቅ ፓርላማ በመውረር የአዲሶቹን  ካቢኔዎች ዕጩነት ፓርላማው ለማጽደቅ የወሰደበትን ረዥም ጊዜ ተቃውመዋል፡፡

የሻዒቶች መምህር የሆኑት ሞቃታዳ ሳዲር ደጋፊዎች የፓርላማውን አጥር በመጣስ ወደ ውስጥ በመዝለቅ የአዳዲስ ሚንስትሮቹን ሹመት ለማጽደቅ ያንገራገሩ የፓርላማ አባላትን ተቃውመዋል፡፡ፓርላማው በሰልፈኞቹ ቁጥጥር ስር መውደቁን ተከትሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን ፓርላማው አቅራቢያ የሚገኘውን የአሜሪካ ኢምባሲ ፖሊሶች በመክበብም በሰልፈኞቹ ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተዘግቧል፡፡

ሰልፈኞቹ ፓርላማውን በወረሩበት ሰዓትም ስብሰባ ለይ የነበሩ የፓርላማ አባላት በሌላ መውጫ በመጠቀም መሸሻቸው ተሰምቷል፡፡ተቃውሞ አቅራቢዎቹ ከፓርላማው በመውጣት ግሪን ዞን ተብሎ የሚታወቀውን ቦታ መቆጣጠራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

መምህሩ ሳዲር የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይዴር አል አባዲ ከአንድ ወገን ብቻ ተመርጠው የተሾሙትን ሚንስትሮች ሁሉን በሚያስማማ መልኩ ለመቀየር የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ሲጠይቁ ቆይተዋል ነገር ግን በፓርላማው ተሰሚነት ያላቸው ኃይሎች የሚንስትሮቹን መለወጥ በመቃወም ሲያጓትቱ ቆይተዋል፡፡

የኢራቁ ፕሬዘዳንት ፉዓድ ማሱም ተቃዋሚዎቹ ፓርላማውን እንዲለቁና የፓርላማ አባላቱ የሚንስትሮቹን ለውጥ እንዲያጸድቁ መጠየቃቸውንም ቢቢሲ አትቷል፡፡

ምንጭ ቢቢሲ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s