አምንስቲ ዮናታን ተስፋዬ ያለቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቅ አሳሰበ

yoni

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ በማህበራዊ ድረ ገጹ (ፌስ ቡክ ) በጻፈው ጽሁፍ ምክንያት የጸረ ሽብር አዋጁ ተጠቅሶ የተከሰሰውን የተቃዋሚ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዮናታን ተስፋዬን እንዲለቁ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ በታህሳስ ወር ለእስር መዳረጉን ያስታወሰው አምንስቲ መደበኛ ክስ ሳይመሰረትበት ረዘም ላሉ ወራቶች በምርመራ ላይ መቆየቱንም ጠቅሷል፡፡መንግስት በክሱ የዮናታን የፌስ ቡክ ላይ ጽሁፎች በሽብርተኝነት የተፈረጀውን የኦነግን አላማ ለማሳካትና አዲስ አበባን ለማስፋት የተያዘውን እቅድ ተገን በማድረግ ብጥብጥ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል፡፡

ዮናታን ተስፋዬ ከኦነግ ጋር ግኑኝነት የለውም ያለው አምንስቲ ክሱ መንግስት ተቃዋሚዎቹን ለማፈን የሚጠቀምበት ዘዴ መሆኑ በስፋት ይታወቃል ብሏል፡፡አምንስቲ አሁንም የጸረ ሽብር አዋጁ ተቃዋሚዎችን ጸጥ ለማሰኘት መንግስት እየተጠቀመበት የሚገኝ ማጥቂያው መሆኑን በዮናታን ላይ የተመሰረተው ክስ ያሳያል በማለት ትችቱን አቅርቧል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሁሉንም ተቃዋሚዎቻቸውን በሽብርተኝነት ይፈርጃሉ ያለው የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው ተቋም ዮናታን በኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ የሚገኘውን የመሬት ቅርምት በመቃወም ሲናገር ቆይቷል ይህ ደግሞ ወንጀል አይደለም››ያሉት የአምንስቲ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሙትሆኒ ዋንዬኪ ናቸው፡፡

‹‹ዮናታንና እንደ እርሱ ሁሉ በተመሳሳይ ሁኔታ ለእስር የተዳረጉ ሰዎችን መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ መፈታት ይኖርባቸዋል››ብለዋል፡፡

”ዋንዬኪ‹‹የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ገለልተኛና ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ ዮናታን በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ቆይታው ቶርቸር ተፈጽሞበት ወይም ጤናማ ባልሆነ አያያዝ መያዙን መመርመር ይኖርባቸዋል››ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡

ምንጭ አምንስቲ ኢንተርናሽናል

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s