የጋዜጦቻችን ዲዛይነር አብነት ረጋሳ ለስደት ተዳረገ

በንተ

ፍኖተ ነጻነት፣የሚልዮኖች ድምጽ፣አዲስ ገጽ ጋዜጦችንና በማህበራዊ ድረ ገጽ ብዛት ላላቸው ዌብ ሳይቶች ብግራፊክስ ዲዛይነርነትና በአንድነት ፓርቲ የወጣቶች ክፍል ሞያዊ አገልግሎት ሲያበረክት የቆየው የፎቶ ግራፍ ጋዜጠኛው አብነት ረጋሳ ለስደት መዳረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አብነት ከአምስት ወራት በፊት ዱባይን ለመጎብኘት የአየር ትኬት ቆርጦ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊበር ሲል በቦሌ አየር መንገድ የጠበቁት ደህንነቶች ፓስፖርቱን በመንጠቅ ስሙ ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ በመኖሩ ከአገር መውጣት እንደማይችል በመንገር እንዲመለስና በየሳምንቱም በአገር ውስጥ መኖሩን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ሪፖርት እንዲያደርግ አዘውት ነበር፡፡

የአንድ ልጅ አባትና ባለትዳር የሆነው የፎቶግራፍ ጋዜጠኛው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ያደረጋቸውን ሰላማዊ ሰልፎች በመከታተል ፎቶ ግራፍ በማንሳትና ቪዲዮ በማዘጋጀት በተለያዮ ዌብ ሳይቶች እንዲሰራጭ የምታደርገው አንተ መሆንህነ ደርሰንበታል በማለት ደህንነቶች ለወራት ሲያስጨንቁት ቆይተዋል፡፡

አብነት በመጨረሻም አገሩንና አፍላ የትዳር ህይወቱን በመተው ለስደት ተዳርጓል፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s