ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በዛምቢያ ድብደባ ተፈጸመባቸው

በዛምቢያ ሉንግዋ መንደር የሚገኙ የጸጥታ ሰራተኞች 34 ኢትዮጵያዊያን የሉንግዋን ድንበር በማቋረጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያመሩ ሲሉ መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

የሉንግዋ ፖሊስ ረዳት ሱፐር ኢንቴንዴንት ማታ ሙሌታና የአገሪቱ የስደተኞች ኮሚሽን መስሪያ ቤት እንዳረጋገጡት ከሆነ ኢትዮጵያዊያኑ የዛምቤዚን ወንዝ በማቋረጥ ወደ ዚምቧቡዌ ከዚያም ወደ ደቡብ አፍሪካ በህገ ወጥ መንገድ ለመግባት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኙ ነበር፡፡

የፖሊስ ኃላፊው 34 ኢትዮጵያዊያን ወንዶች፣ሴቶችና በወጣትነት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን በመግለጽ ወደ ዛምቢያ የገቡት የታንዛኒያን ድንበር በማቋረጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፖሊስ ኃላፊው ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በአካባቢው ነዋሪዎች መደብደባቸውን በመግለጽ አንደኛው ክፉኛ በመደብደቡ በካቶንድዌ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ስደተኞቹ የተደበደቡት ዘራፊዎች ናቸው በሚል ምክንያት መሆኑን የተናገሩት ማታ ሙሌታ ክፉኛ የተደበደበው ወጣት ልማደኛ ገዳይ ይመስላል ተብሎ ነው ይላሉ፡፡ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ዶላር ይዘዋል ተብለው ስለሚገመቱ ለዘራፊዎች የሚጋለጡ መሆናቸው የሚታወቅ በመሆኑም በዛምቢያ ያጋጠማቸው ድብደባም ንብረታቸውን ለመዝረፍ ከተደረገ ሙከራ ተለይቶ አይታይም፡፤

በቅርቡ በኬንያ ናይሮቢ 23 ኢትዮጵያዊያንን የአካባቢው ነዋሪ ዝርፊያና ድብደባ ሊፈጽምባቸው ሲል ፖሊስ በመድረሱ በህይወት ለመትረፍ መብቃታቸው አይዘነጋም፡፡

ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰበት ኢትዮጵያዊ በስተቀር 33ቱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ያስታወቁት ኃላፊው በቀጣይ ቀናቶች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር የሚወሰደውን እርምጃ እንደሚያስታውቁ መናገራቸውን ሉሳካ ታይምስ ዘግቧል፡፡

የሉንጋዋ ወረዳ ኮሚሽነር ያሪኦስ ሲሙኮኮ ኢትዮጵያዊያኑ በወር ውስጥ ሲያዙ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን በማስታወስ ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ ይናገራሉ፡፡ከዚህ ቀደም በማኦዜካ ግዛት ኬላ 16 ኢትዮጵያዊያን መያዛቸውን የሚናገሩት ኮሚሽነሩ ፖሊስ የሰዎች ህገ ወጥ ዝውውር እንዲቀንስ ጠንክሮ መስራትና ነገሮችን በንቃት መከታተል እንደሚገባው አውስተዋል፡፡

ባለፈው ወር በቁጥጥር ስር የዋሉት 16 ኢትዮጵያዊያን የተሳፈሩባትን ቶዮታ ሃይሲ ሚኒባስ ያሽከረክሩ ከነበሩ ሁለት ዛምቢያኖች ጋር ፍርድ ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው 1000 የኬንያ ሺሊንግ ወይም በስድስት ወር እስራት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው መሆኑ አይዘነጋም፡፡

ምንጭ ሉሳካ ታይምስ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s