ያልታሰረ እኮ አይፈታም!

ከታሪኩ ደሳለኝ

“እሺ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ግቢችንን እንዴት አየከው?” “ከግቢያቹ እንዴት ነፃ እንደምትወጡ እየሳብኩ ነው” “ተመስገን አንተ እኮ ነህ ያታሰርከው!” “እኔ ታስሬ አላውቅም የታሰረውስ ሥራዐታቹ ነው ያውም እግር ከወርች እኔ የፃፍኩት ሀገሬን ያሰረው ስርአዐታቹና የስራአቱ አባቶች ከያዛቸው ሀገር የመጥፋት በሽታ እንድትፈቱ እንዲሁም ያልታሰሩ ሰዎችና ያልታሰረ ስርዐት እንዲኖር ነው” “ተው እንጂ በእስር ቤት አጥር ውስጥ ሆነህ አልታሰርኩ ትላለክ እንዴ” “በዚህ አጥር ውስጥማ እናተም ታሳሬ ለመጠበቅ ብላቹሁ ካታሰራቹ ስንት አመታቹ እርግጥ ነው በአካል ከዚህ አጥር ውጪ እንዳልወጣ አድርጋቹሁኛል ሃሳቦቼ ግን የሰራቹሁት አጥር አለገደውም አያግደውምም ይህን ማስቆም የሚችል በየሰዎ ጨንቅላት ውስጥ የሚቆም አጥር መስራት ግን አትችሉም” “ተመስገን ሃሳቦችህ ከእስር ሲያስፈታህ እናያለን ሃስቦችግ ከህመምህ ሲያድኑህ እናያለን” “ያልታሰር እኮ አይፈታም”።
Temesgen Desalegn behindbar

ይህን ንግግር የተነጋገሩት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና የዝዋይ እስር ቤት አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ናቸው። ሚያዝያ 28/08 ዓም አርብ አለት ተመስገን ድጋሚ ወደ ሆስፒታል መሄድ እንደማይችል “ትሄድ መስሎካል!” ብለው የነገሩ ቀን የተነጋገሩት ነው።
እኛም ተመስገን “አትጠብቁ የነሱ ስልጣን አይደለም ታዘው ነው” ያለንን ሳንሰማ በዚህ ሳምንት ሆስፒታል ይወስዱታል በማለት ከዛሬ ነገ እያልን ሳምንቱን ብንገፋም በመጨረሻው ቀን ህክምና እንደማያገኝ ማውቅ ችለናል።

እሁድ ሚያዛ 30/08ዓም በዝዋይ እስር ቤት ከተመስገን ጋር በጠያቂና በተጠያቂ ቦታ ተቀምጠን እየተነጋገርን ነው። በዚህ መካከል ተመስገን ከተቀመጠበት ሁለት ሰው አልፋ ብሎ ጠይም እርጅም በእስፖርት የጠበደለ ሰውነት ያለው ሰው መጥቶ ተቀመጠ። እኔ ከተሜ ጋር ማውራቴን ቀጠልኩ “ህክምናውስ ቀረ ሰዎቹስ እንዴት ናቸው?” አልኩት “ይህን ግዜ ሁለቱ እቃዬን እየበረበሩ ነው አንዱ ደግሞ ይህው” አለኝ ከተሜ ፈንጠር ብሎ የተቀመጠው ግዙፉ ሰውዬ። አየሁት አየኝ። “ይህ የመረጃ ደህነነት አባል የነበረ ነው” አለኝ ነው በማለት እራሴን ነቀነኩ። እኔ ከተቀመጥኩበት አጠገብ: አንድ ቀጠን ረዘም የለ ሰው መጥቶ በመቀመጥ ከሰውዬው ጋር ማውራት ጀመረ። ጠያቂውን የማውቀው መሰለኝ ጠያቂው የያዘውን እቃ ለተጠያቂው አቀባለው። ወደ ተሜ ዞሬ “እና እንዴት ነው?” አልኩት “የነበረኝን ቁራጭ ወረቀትና እስክርቤቶ ወሰደውብኝል አንገቴ ቆርጠው እስኪወስዱት ደረስ ግን አይስቆሙኝም” አለኝ ደነገጥኩ። አውቃለሁ ለሀገሬ ስል ያለውን ሁሉ ተሜ እስከመጨረሻው እንደሚያደርግ ግን ሲለኝ ደነገጥኩ። ደንግጪም ዝም አልኩኝ። “በል ሂድ እንዳንዳይመሽብህ” አለኝ
ለስንብት ስነሳ የተሜ ዐይኑ ከኔ አለፍ ብሎ የተቀመጠው የመረጃ ደህነት የነበረውን ሊጠየቅ የመጣውን ሰው ሲመለከት አየሁ አይን ተከትዬ ሳይ ሰውዬው ከደረገው ሱሪ ስር አምልጡ የወጣውን የውታደር ዩኔፎርም ወደ ውስጥ ለመደበቅ ሲታገል ተመለከትኩ። አሁን ሰውዬውን አስታወስኩት “አውቀዋለሁ በር ላይ ከሚፈትሹት አንዱ ወታደር ነው” አልኩት ተሜ ምንም አይነት ስሜት ሳይሰማው እራሱን ነቀነቆ አቅፎ ሰለምታ ሰጥቶኝ ሄደ ከጀርባው ተመለከትኩት የደረገው አረንጓዴ ቤጫ ቀይ ጥለት ያለው እስካርቭ እየተወዛወዘች ነው ለቭንዲራወም ለተሜም ከአንገቴ ጉንበስ ብዬ ስላምታ ሰጥቼ ወጣሁ ።

ከእስር ቤቱ ስወጣ ግን የመረጃ ደህንነት አባሉና የጠያቂው ሁኔታ ግራ እያገባኝ ነው።

በዝዋይ እስር ቤት ጠያቄ መጀመሪያ የሚያጠይቀውን ሰው ስም አፅፎ መጥቶ ያስጠራል እንጂ ተጠያቂው ቀደሞ አይመጣም ወይ በስልክ ወይ በሬዲዬ ጠያቂው ካልተጠረ በቀር ቀድሞ አይደርስም ሌላው ደግሞ ጠያቂ ሲመጣ በጠያቂና በተጠያቂ መካከል የሚቆሙት ወታደሮች የመጣከውን ወረቀት ለሚጠሩ ሰዎች እንድትሰጥ ያደርጉሃል እንጂ መጥተክ ከገኘከው ተጠያቂ ጋር እንድታወራ አይፈቅዱልህም እንዲሁም አንድ ጠያቂ የመጣውን እቃ በር ላይ ቢፈተሽም እነዚህ ወታደሮቹም ድጋሚ ፈትሸው ነው ለተጠያቂው የሚሰጠት። እንግዲህ ከለይ የጠቀስኩት ነገሮችን በመረጃ ደህነት አባል ተጠያቂ እና በፍታሽ ወታደር ጠያቂ መካከል ሲፈፀመ አልተመለከትኩኝም።

እንደው የመብት ሁሉ ጌታ ነኝ የሚል ስርዓት እንደዚህ አይነት ነገር ሲፈፅም ስትመለከት ታዝናለህ ትናደዳለህ ትገረማለክ ምን እንደሚሰማህ አታውቀውም። ብቻ የሆነው ሁሉ ሆኖ አንድ ቀን ተሰፋ አደርጋለሁ ሀገራችን ለሚያሰቡ ሰዎች የሰራችውን እስር ቤት ሁሉ እንደምታፈርስ።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s