አምንስቲ በለንደን ለኢትዮጵያ ኢምባሲ እስክንድር ነጋን የተመለከተ አቤቱታ ያቀርባል

free

 

አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል የፕሬስ ፍሪደም ቀንን ምክንያት በማድረግ ግንቦት 15/2008 ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት የህሊና እስረኛ የሆነው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንደሚጠይቅ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በእንግሊዝ የሚገኙ የአምንስቲ ኢንተርናሽናል አባላትና ደጋፊዎች ከወዲሁ እስክንድር ነጋ ይፈታ ዘንድ ለመጠየቅና እስካሁን ድረስ እስክንድር ነጋ በወህኒ ቤት እንዲቆይ መደረጉ እንደሚያሳስባቸው በመግለጽ ፊርማ ማሰባሰብና ካርዶችን መላክ መጀመራቸው ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን በማሰርና ህዝቡን መረጃ እንዳያገኝ እያገደው መሆኑን ዘወትር በሚያወጣቸው ሪፖርቶች አጥብቆ የሚተቸው አምንስቲ ባለፈው ዓመትም በለንደን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት አባላቱ በመገኘት ጋዜጠኛ እስክንድርና ሌሎች ጋዜጠኞች እንዲፈቱ መጠየቁ አይዘነጋም፡፡

አምንስቲ ከኢምባሲውም ሆነ ከኢትዮጵያ መንግስት ቀና ምላሽ ባያገኝም ዘንድሮም ‹‹የህሊና እስረኛው›› እንዲፈታ ከመጠየቅ ወደኋላ እንደማይል አስታውቋል፡፡

‹‹የሰበሰብናቸውን ካርዶችና ፊርማዎች በአካል በመገኘት ለአምባሳደሩ በመስጠት እስክንድር እስኪፈታ ድረስ ይህንን ማድረጋችንን እንደማናቋርጥ እንነግራቸዋለን››ብሏል፡፡

ምንጭ አምንስቲ ኢንተርናሽናል

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s