በጂንካ ህዝባዊ ብሶቱ እየተንተከተከ ነው–ሳይቃጠል በቅጠል (ግርማ በቀለ)

e189b0e18ca0e1889be18982e18b8ee189bd-e18aa8e18ba8e188b5e189a5e18aa8e189b5-e18aace1888be18b8ee189bd-e18b88e18bb0-e18c82e18a95e18aab

በደቡብ ኦሞ የህዝቡን ‹‹ ህገመንግስታዊ መብት ይከበር እና ህጋዊ አሰራር ይስፈን ›› ጥያቄ በማስፈራራትና በእስራት ለማፈን አልተቻለም፡፡
በደቡብ ኦሞ ዋና ከተማ -ጂንካ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ዓለማዬሁ ቦዲ ከከተማው ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር‹‹ መልካም አስተዳደርና ልማት ›› በሚል ግንቦት 10/2008 ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ በአስተዳደሩ ላይ ያለውን ምሬት የገለጸ ሲሆን አስተዳዳሪው ለማስፈራራት የተለያዩ የውንጀላና የፍረጃ ቃላት ቢጠቀሙም ህዝቡ በጄ ሳይል የመብትና ዲሞክራሲ ጥያቄዎችን አቅርቧል፡፡ ከቀረቡት አንሏር ጥያቄዎች ውስጥ–
1ኛ/ ጠቅላይ ሚ/ሩ ህጋዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ባይመረጡም በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላያ እናሳትፋቸዋለን በማለት መንግስታቸውን አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በዞናችን እስካሁን ይህ ሲተገበር አላየንም፣ ይልቁንም በተቃራኒው ህዝቡን ለማፈን፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በሃሰት በመወንጀል፣ በመፈረጅና ለማስፈራራትና ከእንቅስቃሴኣቸው ለመገደብ አጠንክራችሁ እየሰራችሁ ነው፡፡ አሁን ከቀረበው የውይይት አጀንዳ አንጻር በቀጣይ ህጋዊ ተቃዋሚ ድርጅቶችን በዞናችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለማሳተፍ ምን አስባችኋል ?
2ኛ/ ስለ ህጋዊነትና ህገመንግስታዊነት ደጋግማችሁ ትናገራላችሁ፤ በዚህ ረገድ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አወቄ አይኬ ሹመት እንዴት ይታያል፡፡ አቶ አወቄ ለክልል ም/ቤት አልተመረጡም ፣ የዞንና ወረዳ ምርጫ አልተካሄደም፡፡ ታዲያ አቶ አወቄ በምንና ማንን ወክለው ነው የተሾሙት ? ይህ በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 87/ሐ መሰረት ህጋዊና አግባብ ነውን ?
3ኛ/ ልክ የዛሬ ወር የኦህዲኅ አባላትና አቶ ስለሺ ጌታቸው አዋሳ ታስረው በነበረበት ለተነሳ ጥያቄ ‹‹ …በተጨባጭ ከጦር መሳሪያና ከኢሌክትሮኒክስ የመገናኛ መሳሪያ ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዘው ነው የታሰሩት… ›› ብለው ነበር፡፡ ይህ ተሳሳተ መረጃና ባዶ ውንጀላ በመሆኑ ሰዎቹ ይህን ባሉ በሶስተኛው ቀን ተፈተዋል፡፡ በዚህ ላይ ህዝቡን ይቅርታ ሊጠይቁ አይገባምን?……
የዞኑ አስተዳዳሪ ግን ጉዳዩ ካፈርኩ አይመልሰኝ፣ ሆኖባቸው ‹‹ያደቆነ ሠይጣን ሳያቀስስ አይለቅም›› እንዲሉ በክህደታቸውና ማስፈራራታቸው ቀጥለውበታል፡፡ እንዲህ በማለት ‹‹ …አሁንም ቢሆን ለአሸባሪዎች ከዞኑ ድጋፍ ማድረጋቸው እውነት ነው፤ ከአርባ ምንጭ የመጡ ሁለት ወጣቶች በ28/08/08 ከዞናችን ተይዘው መወሰዳቸው የዚህ ማረጋገጫ ነው፣ አሁንም አሸባሪዎችን ማሳደዱ ይቀጥላል፤…››
እነዚህ ታስረው ተወሰዱ የተባሉት ወጣቶች እነማን ናቸው፣ ለምንስ መጡ ?የሚለውን ስንመለከት ጉዳዩን ግልጽ ያደርገዋል፡፡ የጂንካ ፖሊስ ባልደረባ የሆነው ም/ሳጅን ወንድማገኝ ቦጋለ በማረፉ አርባ ምንጭ የሚኖረው ወንድሙ ወጣት ደምመላሽ ቦጋለ ከጓደኛው ወጣት ብራዚል እንግዳ ጋር ለለቅሶ ወደ ጂንካ ይመጣሉ ፡፡ ከአርባምንጭ በመምጣታቸው ብቻ ባለፈው አርባምንጭ በተፈጠረውና አርበኞች ግንቦት 7 ኃላፊነቱን በወሰደው ኦፕሬሽን ተጠርጥረው ከለቅሶ ቤት ተይዘው ተወሰዱ፡፡ ይህ ታዲያ የአሳሪዎችን ጭካኔና መደናበር ከማሳየት ሌላ ቀድሞ ከታሰሩት እን ስለሺ ጌታቸው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ወቼ ጉድ– ለወንድም ለቅሶ ማይደረስበት ዘመን //
ያም ሆነ ይህ አስተዳዳሪውና ምክትላቸው በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ ለሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች በማስፈራራትና ሲያልፍም በማሰር ለማፈን ቢሞክሩም ህዝቡ ፈርቶ ጥያቄዎችን ከማንሳት ወደኋላ አላለም፣ ወደፊትም አይልም፡፡
እናም እንላለን— አፈና ለጥያቄዎች መልስና ለችግሮቹ መፍትሄ አይሆንም፤ አስተዳዳሪዎች ከእብለትና እብሪት ወጥተው ለህዝቡ ሰላማዊና ህጋዊ ጥያቄ ጆሮ ይስጡ፣ ከህዝቡ ጋር ሆነው መፍትሄ ያብጁ መልእክታችን ነው፡፡ ያለበለዚያ ዛሬ በጊዚያዊ ጥቅም ተደልሎና በኃይል ተመክቶ በጉዳይ ፈጻሚነትና አስፈጻሚነት የሚደረገው ሁሉ ነገ ‹‹ ታዝዤ ነው ፣ከላይ በመጣ መመሪያ ነው…›› ቢሉ በዋነኛነት ህገ መንግስታዊና ህጋዊው ስልጣናቸውና ኃላፊነታቸው የዞኑን ህዝብ መብትና ጥቅም ማስከበር ነውና ከወንጀልና ተጠያቂነት ነጻ አያደርግምና ‹‹ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው›› የሚለውን የአበው ብህል አስታውሰን ልብ ለው ልብ እንዲል እንመክራለን፡፡
እስከ ድሉ ቀን በጎ- በጎውን ያሳስበን፣ ያሰራን፣ የሚበጀውን ያሰማን፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s