በምስራቅ ሐረርጌ ቆቦ ከተማ የሕዝብ ቁጣ በአደባባይ ተሰማ – ነቀምት ከተማ በአጋዚ ጦር ተከባለች

ቆቦ ከተማ (ምስራቅ ሀረርጌ)

ጋብ ብሎ የነበረውና በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ሲደረግ የነበረው የሕዝብ ቁጣ ሰሞኑን እየተቀጣጠለ ሲሆን ዛሬ ጠዋት ደግሞ በምስራቅ ሐረርጌ ቆቦ ከተማ ሕዝብ ተቃውሞን ለማሰማት አደባባይ ወጣ::

በቆቦ በተደረገው ተቃውሞ ሕዝቡ የኦህ ዴድ/ኢህአዴግ አስተዳደርን ክፉኛ ሲቃወም የነበረ ሲሆን በዚህ ተቃውሞ በአብዛኛው የተሳተፉት ወጣቶች እና ሴቶች እንደነበሩም የአካባቢው የዜና ምንጮች አስታውቀዋል::

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያያዞ በተነሳውና ጋብ ብሎ ቆይቶ እንደገና ባገረሸው በዚሁ ተቃውሞ ፌደራል ፖሊሶች እንዲህ ያለውን ሰላማዊ የሕዝብ ቁጣ ለማስቆም ጥይት ከመተኮስ እስከመግደል ያለፈ እርምጃ እንዲወስዱ ት ዕዛዝ መተላለፉን ዘሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘግቧ አይዘነጋም::

በምስራቅ ሐረርጌ የተደረገውን ሕዝባዊ ቁጣ ፌደራል ፖሊስ እርምጃ የወሰደ መሆኑ ሲታወቅ እስካሁን የተጎዱ ሰዎች ዘ-ሐበሻ እንዳሉ ለማረጋገጥ ሞክራ አልተሳካላትም::

በሌላ በኩል የአጋዚ ጦር የነቀምቴን አደባባዮች እንደወረረው ከስፍራው የመጡ መረጃዎች ጠቁመዋል:: ሰር ዓቱ ከግምቦት 20 በዓል ጋር በተያያዘ ሕዝባዊ አመጽ ይነሳል በሚል ሕዝቡን ለማሸበር ጠመንጃ የታጠቁ በርካታ ወታደሮችን በየአደባባዩ ያሰማራ ሲሆን ከተማዋ በውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ የደረሰን መረጃ ያስረዳል::

ነቀምቴ ከተማን ከወረሯት የአጋዚ ጦር አባላት

 

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s