የኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ በኢንተርኔት ተሰራጨ

fetena 44

fetena

fetena2

በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ሰኞ እንደሚካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ሲሆን ሆኖም ግን ፈተናው ተሰርቆ ቀድሞ በኢንተርኔት መሰራጨቱ ታወቀ::

በDropbox አማካኝነት እንዲሁም በፌስቡክ እና በሌሎች ሶሻል ሚድያዎች ፈተናው ተሰራጭቶ የሚገኝ ሲሆን መንግስት ግን ምንም ዓይነት ፈተና አልተሰረቀም ሲል በሚያዛቸው ሚዲያዎቹ አውጇል::
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን “የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ነገ ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ.ም ይሰጣል ፡፡ ይሁንና ፈተና ተሰርቋልና ሌሎች መሰል አሉባልታዎች እየተናፈሱ መሆናቸው ተደርሶበታል፡፡ ነገር ግን የተሰረቀ ፈተና እንደሌለ፣ እንዲሁም በፈተና ዝግጅትና ስርጭት ላይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለ በመሆኑ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች በአሉባልታ ሳይረበሹ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡” ሲል ለማሰባበል የዘገበ ቢሆንም አብዛኛው የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው በሶሻል ሚዲያዎች ተለቀዋል::

በተለይም ፈተናው የተሰራጨበት የDropbox ሊንክ በከፍተኛ ትራፊክ (ጎብኚዎች) መጨናነቅ ምክንያት ለጊዜው መታገዱ ቢገለጽም ብዙዎች ፈተናዎቹን ከነመልሱ በሶሻል ሚዲያዎች ማሰራጨታቸውን ቀጥለዋል:: ለጊዜው ፈተናውን ለማየት Dropbox ሲገቡ የሚከተለውን ያሳያል::

This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s