በጾረና፣ ባድመና ዛላንበሳ ግምባር የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ተፋጠዋል | የቦምብ ፍንዳታ ተሰምቷል

በጾረና ግምባር በኩል የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች በብዛት እየሰፈሩ መሆኑ ተሰማ:: ከትናንት በስቲያ ምሽት ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው የሁለቱ ሃገራት ግጭት ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ የተደረገበትና አብዛኛውም ጊዜ በስለላ ላይ ያተኮረ ግጭት እንደነበር

ሞርታር እና አርፒጂን የተሰኙ በጦርነት ላይ በጣም ከባድ የማይባሉ መሳሪያዎች በዚህ የሁለቱ ሃገራት ግጭት ላይ በጥቅም ላይ እንደዋለ የደረሰን መረጃ ሲያስረዳ ዓዲ መስገነን; አሃራንንና ቁኒቁንቶን በተሰኙ ቦታዎች ከትናንት ጀምሮ የተኩስ ልውውጥና ግጭቱ እንደተካረረ ምንጮች ገልጸዋል::

ወታደራዊ ምንጮች እንደሚሉት ሁለቱም ሃገራት በአሁኑ ወቅት ጦራቸውን ወደ ድንበሮቹ አስጠግጠዋል:: ማምሻውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስተር ባወጣው ባለ 6 መስመር አጭር መግለጫው የሕወሓት መንግስት በጾረና በኩል ወረራና ጥቃት ፈጽሞብኛል ሲል ከሷል::

ከትግራይ ክልል  መረዳት እንደተቻለው በኢትዮጵያና በኤርትራ ወታደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ የተሰማው በጾረና በኩል ብቻ ሳይሆን በባድመ እና በዛላንበሳ ግንባሮችም ጭምር ነው:: በተለይም በባድመና በዛላምበሳ የቦምብ ድምጾች ሁሉ ይሰሙ እንደነበር ምንጮቹ አስረድተውናል::

ኤርትራ የኢትዮጵያ መንግስት በጾረና በኩል ወረረኝ ስትል ብትከስም በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስትም ቢሆን በአንጻሩ የኤርትራ መንግስት በተለያዩ ድንበሮች በኩል እየተነኮሰኝ ነው ሲል መቆየቱ ይታወሳል::

ትናንት ማምሻውን በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን ሲያጓጉዝ እንደነበር የተመለከ ገልጸዋል::

This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s